September 16, 2024 – Konjit Sitotaw 

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በተለይ በቻይና ያላትን የሰሊጥ የገበያ ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጣች መኾኗን መስማቱን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም ላኪዎች ማኅበር፣ ኢትዮጵያ ከአስር ዓመት በፊት በቻይና ገበያ የነበራት 50 በመቶ የሰሊጥ ገበያ ድርሻ ባኹኑ ወቅት ወደ አምስት በመቶ ማሽቆልቆሉን እንደገለጠ ዘገባው አመልክቷል።

ለሰሊጥ የውጪ ገበያ ማሽቆልቆል ምክንያቶቹ፣ ከምርት አቅርቦት ሰንሰለትና ከምርታማነት ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደኾኑ ዘገባው ማኅበሩ ተናግሯል ተብሏል።

ሰሊጥ ባብዛኛው በማምረት የሚታወቁት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሁመራ እና መተማ አካባቢዎች ናቸው።