September 17, 2024 

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ማባረሩና ከነበራቸው ድርጅታዊ ሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ።

ድርጅቱ መስከረም 6/2017 ዓ.ም አካሄድኩት ያለውን ስብሰባ አስመልክቶ ባወጣው ባለ ሦስት ገፅ መግለጫ :-

1. አቶ ጌታቸው ረዳ
2. አቶ በየነ ምክሩ
3. ፕ/ር ክንደያ ገ/ሂወት
4. ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፈይ
5. ወ/ሮ ኣልማዝ ገ/ፃዲቕ
6. አቶ ረዳኢ ሓለፎም
7. ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ
8. አቶ ኢሳያስ ታደሰ
9. አቶ ሰለሞን መዓሾ
10. አቶ ሺሻይ መረሳ
11. ዶ/ር ገ/ሂወት ገ/ሄር
12. አቶ ርስቁ አለማው
13. አቶ ሃፍቱ ኪሮስ
14. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ
15. አቶ ሩፋኤል ሽፋረ
16. አቶ ነጋ ኣሰፋ

ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነት ” አባርሪያችኃለሁ ” ብሏል።

የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈገውና የድርጅቱ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳና በርካታ የማእከለዊ ኮሚቴ አባላት ” ህገወጥ ” ያሉትን 14ኛ ጉባኤ በማካሄድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል መልሶ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።