ፍሬከናፍር ‹‹አገር በእልህና በትንግርት መምራት አይቻልም›› ነፍስ ኄር በየነ ጴጥሮስ (ፕሮፌሰር)

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ቀን: September 18, 2024

የአዲሱን ዓመት ቅበላ አስመልክቶ ከ‹‹ዘ ሪፖርተር›› ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የተናገሩት፡፡ አውቆ የተኛን ሰው መቀስቀስ እንደማይቻለው ሁሉ፣ አገርን በትንግርት አትመራም ያሉት አንጋፋው የሥነ ሕይወት ፕሮፌሰርና ፖለቲከኛው፣ ‹‹በአዲሱ ዓመት ምን ተስፋ ያደርጋሉ?›› ተብለው ለተጠየቁትም የሰጡት ምላሽም፣ ‹‹እኔ በተስፋ አይደለም የምኖረው ለቀጣይ ዓመት ከየትኛው ሐሳብ የትኛው ይበልጣል የሚለውን እያሰላሰልኩኝ ነው የምንኖረው፤›› ብለዋል፡፡