September 19, 2024 – Konjit Sitotaw 

የደብረፅዮን ቡድን ለስልጣኑ ሲል የትግራይ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል ሲል የጌታቸው ረዳ ቡድን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

አባላቱ አክለውም የትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ለስልጣኑ ሲል ወደ መካድ ደርሷል ሲል ከሰዋል።

የጌታቸው ቡድን መግለጫው የደብረፅዮን(ዶ/ር) ቡድን ማንኛውም አካል ላይ ውሳኔ የማሳለፍ ሆነ እርምጃ የመውሰድ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው ለህዝባችን እና ለአባላቶቻችን ማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

የአቶ ጌታቸው ቡድን ከፌደራል መንግስት ጋር የህወሓት ህጋዊ ሰውነትን ለመመለስ በምናደርገው ፓለቲካዊ ድርድር መላው አባላችን እና ደጋፊ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን ብሏል።