ዝንቅ ‹‹ሄቦ›› የየም የዘመን መለወጫ
ቀን: September 22, 2024
ሄቦ ከጭጋግና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሻገሪያ የም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡ በዓሉ የአዲስ ዓመት መባቻ በመሆኑ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ተወላጆች ከወላጆቻቸው ጋር የሚገናኙበት እንደሆነ ይነገራል፡፡ የዘንድሮው የሄቦ በዓል መስከረም 20 እና 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በዞኑ ዋና ከተማ ሳጃ እንደሚከበር የየም ዞን የባህልና ቱሪዝም መሥሪያ ቤት አስታውቋል፡፡