Mengistu Musie 

የኢትይጵያዊነት ብሔራዊ ማንነትንም ነው!!

==============================

የሐገር ሉአላዊነትን፤ ዳርድንበር ሀገራዊ አንድነት የማይገባቸው የመንደር ዘረኛ መሪወች ለአለፉት 35 አመታት በእነሱ ይሁንታ ትልቅ የባህር በር አሳልፈው ሰጡ። ሁለት ወንድማማች/እህታማማች ሕዝብን አለያዩ። ዞረው ተመልሰው ባነሱት ጦርነት 100,000 ሽሆችን የአንድ ሐገር ሕዝባችንን አጨራረሱ። ሐገሬ ብሎ ይኖር የነበረውን ዜጋ አይደለህም በሚል ጨርቅ ማቁን ሳይዝ ቤት ንብረቱን ትቶ ተገዶ እንዲሄድ አደረጉ።

ላለፉት 40 አመታት ደግሞ ሐገራቸውን ኢትዮጵያን ኢምፓየር ናት እንገነጠላለን ሲሉ መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የሐገር ሉአላዊነት እና ብሔራዊ አንድነት ነጻነት የሚባሉት ቁልፍ የአንድ ሐገር ስነልቦናዊ እና ማንነታዊ ብሔራዊ ስሜት የነፍጠኝነት አስተሳሰብ ትምክህት፤ አሀዳዊነት ወዘተ በሚል የደንቆሮ አስተሳሰባቸው እንወክለዋለን ከሚሉት ሕዝብ ስነልቦታ አስፍቀው የመንደርተኝነት አስተሳሰብ አላበሱት። ትውልዱ ዛሬ ሐረር ብትወረር ምናገባኝ። አፋር ብትያዝ ምናገባኝ እንዲል አደረጉት። ለዚህ ዋና ማሳያ ዛሬ ዛላንበሳ ተያዘ ብለው ሲናገሩ ለመሆኑ በምእራባዊ ጎንደር በሱዳን የተወሰደው መሬት የማነው ሲባሉ የነፍጠኞች የሚል መልስ እንደሚሰጡ ጥርጥር የለውም። እናም ያሰፊ መሬት ተይዞ እስከዚህ ቀንም በዝምታ ድባብ ውስጥ አሉ/አለን።

እነዚህ ዘረኛ መሪወች የፈጠሩት ስርአት እና ጦራቸው እስከ ተዋጊ ጀቶች እና ታንክ እና ዙ 23 በሕዝባቸው ላይ ሲያዘንቡ የማይሰማቸው ጠላት ማለት የራስ ዜጋ የሌላው ክልል ሰው እያሉ ከልሂቅ እስከደቂቅ ደናቁርት ካድሬወች ያስተጋቡታል። ጀግንነትን በራስ ዜጋ ግድያ ይተረጉሙታል።

በነሱ ዙ 23 እና መትረጌስ ላለመሞት እራሱን ተከላክሎ ትጥቃቸውን አስወርዶ ሲመልሳቸው በሰላማዊው ዜጋ ሂሳብ ያወራርዳሉ። ሰላማዊ ዜጎችን አውጥተው ይረሽናሉ። ከዳባት እስከ ጎንደር። ከባህርዳር እስከ መራዊ፤ ጅጋ እና ደብረማርቆስ። ከደብረብርሐን እስከ ደሴ ያካሄዱት ፍጅት አፈ ታሪክ አይደለም የሰበአዊ መብት ተሟጋች የአገር ውስጥ እና አለማቀፍ ማህበራት የዘገቡት የአመታት ሳይሆን የአሁን ታሪካችን ነው።

ይህን ያየ የሩቅም የቅርብም ጠላት ተጠራርቶ ቢመጣ ፍርዱ በማን ይሆን? ዜጎች ከዘረኞች ጥይት ለማምለጥ መከራቸውን የሚያዩበት ግዜ ላይ ነን። ስለታሪካዊ የሩቅም የቅርብም ጠላቶቻቸው ተጠራርተው ዳር ድንበር ላይ መስፈራቸውን እንዴት ይወቁ?

ለብዙ መቶወች አመታት ደርቡሽ (ሱዳን) አቅሟን አውቃ እና ተጠንቅቃ መኖሯ ግልጽ ታሪክ ነው። ዩሐንስ አንገታቸውን የሰጡባት ድንበር ተክለሐይማኖት ልጃቸውን ወ/ሮ ሰብለወንጌልን የተነጠቁባት ዳር ድንበር ከተደፈረች እና በዘመናዊው ደርቡሽ ከተያዘች አመት ሁለት እና ሦስት አመታት ተቆጥረዋል። ይህ አይነቱ መንግስት ነው ዛሬ ዛላንበሳን ያስረከበ። የዚያኛው መንደር ሰወችም ጠፍጥፎ የሰራቸውን አሁንም ጠላት ሳይሉ በልምምጥ እርቅ እና ንግግር ላይ ነን እያሉ ባለበት ነው ዛላንበሳ ተያዘ የሚሉን። ለቃቂውም ሆነ ተያዘብኝ ባዩ መንደርተኛ ሐገርን ሳይሆን ዛሬም ትናንትም ስርአቱን አበጅተው ሲሰሩት ጀምሮ የነገሩን እና በህግ እና ደንብ በአንቀጽ VIII ህገመንግስታቸው ያሰፈሩት የሏላዊነት ትርጓሜ “ብሔር/ሄረሰቦች እና ሕዝቦች” ይላል። እንዲህ የተምታታ ትርጓሜ ብቻ አይደለም ችግር ፈጣሪው። ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜትን የአማራ ትምክህተኝነት በሚል ከሚወክሉት ሕዝብ ስነልቦና ፍቀው ያወጡት እና ዛሬ በአውላላ ሜዳ የቅርብ የሩቅ ጠላት ተጠራርቶ ሲመጣ ያን የማይወዱትን ፍቀው ከየዜጋው ልቦና ያስወገዱትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስሜት እንዴት መመለስ ይቻላል ነው። ይህ የኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ግን በነሱ ትርጓሜ “አሐዳዊነት” ብለውታል። ጠላቶቻችን ግን ይፈሩት ያከብሩት የነበረው ያ በደናቁርቱ “አሐዳዊነት” የተባለው ከሁለት ሦስት ትውልድ እንዲፋቅ በመሆኑ ዛሬ የሚሰጉት የሚፈሩት ባለመኖሩ ዛላንበሳ የምእራብ ጎንደር፤ ነገ ሐረር ባሌ ወዘተ ን። ለመያዝ ቢደፋፈሩ የሚገርም አይደለም።

ባለፈው ሕዳር 2016 ኢሕአፓወች ሰላም ይስፈን። ሰራዊቱ የሐገሩን ዜጋ አይግደል ወደካምፑ ይመለስ በሚል የጠሩት የሰላማዊ ሰልፍ የተቋጨው ሐሳቡን አፍላቂ ለሐገር ተቆርቋሪወችን አዋሽ አርባ በመላክ እና በማፈን ነበር። አሁንም ያለቅድመ ሁኔታ ዜጋን እየገደለ ያለ ሰራዊት በአስቸኳይ ከክልሉ ይውጣ ስራው ዳር ድንበር እንጅ ኢትዮጵያን ከውስጥ ማፍረስ አይደለም እንላለን።