
Wednesday, 02 October 2024 16:01
Written by Administrator

በቅርቡ የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመው የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።
የገንዘብ ሚኒስቴር መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው፤ ዶ/ር እመቤት መለሰ ከጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።
ዶ/ር እመቤት፣ የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸውም በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስትራቴጂ ፕላኒንግና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡
የፖሊሲ ባንኩን ላለፉት 4 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት ዶ/ር ዮሐንስ አያለዉ በግል ምክንያት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ካስታወቁ በኋላ፣ የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ በቅርቡ መሾማቸው ይታወሳል።