October 8, 2024 

የአብይ የጦር ግንባሮች እየተመቱ ነው!! ( ዶ/ር መንግስቱ ሙሴ )

=================

የዳሞቱ 5ኛው ክፍለ ጦር የፋሽስቱን የማሰልጠኛ እና የጦር ማሰማሪያ ተቋም ብርሸለቆን እንደከበበ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። ጀግኖች በታላቅ ተጋድሎ እና መስዋእትነት ድል እየመቱት ነው።

የኢትዮጵያ ጣልያን ጦርነት ከታሪክ የወሰድሁት ትዝ አለኝ። የሞሶሎኒ ትልቆቹ የጦር ምሽጎች ከጎንደር ቀጥሎ ዳንግላ፤ እንጅባራ እና ቡሬ ነበሩ:: የምስራቅ አፍሪካ የጣሊያን ቅኝ ግዛቶች አዛዥ ጄኔራል ዩጎ ካቫሊሮ እና ጄኔራል ጋሊያና የድንገተኛ ማፈግፈግ በማረግ የዳንግላን እና የቡሬን ምሽግ ጦር ሜዳ በትነው እንደሸሹት። ዛሬ ትልቁ የፋሽስት ማሰልጠኛ እና ማሰማሪያ ካምፕ በአርበኛው የዳሞት 5ኛ ክፍለጦር እየተወቃ ሲሆን። ሌላው ትልቅ የጦር ሰፈሩ የዳንግላው መኮድም በተመሳሳይ በሦስተኛው ክፍለ ጦር ከበባ ላይ መሆኑን እየሰማን ነው።

እኛም እንላለን ሕዝብን ማቸነፍ በታሪክ የለም ሆኖም አያውቅም የከፋ የስልት እና የስትራቴጅ ስህተት ካልተደረገ። እናም የጠባቡ እና ጽንፈኛው ብሔርተኛ የአብይ አህመድ፤ የብርሐኑ ጁላ ዘመቻ እየተሰበረ መሆኑን አሳይ ሁኔታወች ተከስተዋል። ጽናት እና ክብር ለተገፋው የአማራ ሕዝብ ይሁን!!! ( ዶ/ር መንግስቱ ሙሴ )