
Mengistu Musie
የበአዴኑ እና የ Forum-84 መጋዣ አዲስ ስልጣን
ከውጭ ጉዳይ ወደ ጉልት ተራ
==================
ለማነኛውም ሰውየው አዲስ አይደለም የጫኑትን ያህል የሚጫን አጋሰስ ነው። ታሪኩም ዝብርቅርቅ ክህደት፤ ቦቅቧቃነት ልክ የለሽ አድርባይ (ባንዳ) የምንለው አይነት ሰው እንደሆነ ብዙ መጓዝ አያስፈልግም። በ1971 ዓም ነው ትፋት ቅርሻቱን ደግሞ ልሶ ሊፋለመው የወጣውን አገዛዝ ይቅርታ ጠይቆ አዘዞ መጠለያ ጣቢያ የተገኘው። የት ይደርሳል ያልነው ወይፈን ቆዳው ከልኳንዳ ደጃፍ ተገኘ የሚባለው አይነት ማለት ነው።
ስንት ጀግኖች የተሰውለትን ትግል ካስጨነገፉት ቦቅቧቆች አንዱ ዛሬ ያነን ከነጋሶ ጊዳዳ እስከ ወይዘሮዋ ይዘውት የነበሩትን ወና (ባዶ ስልጣን) ተረክቧል። አንድ ሰሞን ያኔ ህወሓት አዲስ አበባ ስትገባ እጅ እንደሰጠ ብታውቅም ጓደኞቹ ከበለሳ እና ከጠለምት ክደው እና አያሌ ታጋዮችን አውላላ ሜዳ አጋልጠው ከህወሓት ቤት የገቡትን እነ በረከት፤ ህላዊ፤ ታደሰን በሚያውቅበት የክህደት እና አድርብየ ስልቱ የተለጠፈ።
እነሱም ያው ትውልድን ክደው አያሌ ታጋይ አስጨርሰው እነዚያ ተርብ ታጋዮች በግራ በቀኝ በጠባብ ብሔርተኛዋ ህወሓት እና በገንጣዩ ሻብያ ጥይት ያለቁትን የቃል ኪዳን ጓዶቻቸውን ለጠባቧ ምንደኛ ህሊናቸውን እስከ ሁለንተናቸው ሸጠው አዲስ አበባ የገቡት ምስለኔወችን የተደባለቀው መጋዣም ያው የነሱ ውላጅ ሰለነበር ህወሓትን ለማስደሰት Forum-84 በሚል የያኔ መጋዦች ስብስብ ስም የስልጣን እና ገንዘብ ፍርፋሪ ለማግኘት የተጠጋው።
ባንዳነት ከሰውነት ውጭ ነው እና ዛሬም ትናንትም በማይጮ ትውልድም በታሪክ እንዳየነው፤ በተግባር እንደታዘብነው ስለ ሆድ እንጅ ስለየራስ ክብር እና ነጻነት የማይጨነቅ በመሆኑ የኢሕዴን ምስለኔወች በህወሓት ትእዛዝ አይናቸውን አጥበው በቀናት ከህብረ ብሔራዊነት ወደ አማራነት ተለወጡ እራሳቸውንም በአዴን ብለው በታሪክ ፊት ያስደነገጠ የባንዳነት ልክየለሽ ታሪክ አስመዘገቡ። የደቡቡ ተወላጁ ተፈራ ዋለዋ፤ የትግራዩ ህላዊ ዮሴፍ የኤርትራ ትውልድ ያለው በረከት ስምኦ እና የኦሮሞው አዲሱ ወዘተ የአማራ ድርጅት በህወሓት ትእዛዝ ሲመሰርቱ ሀፍረት የሚባል አንዳች የሰውነት ባህርይ አላሳዩም። ያገሬ ሰው ሌላ የሚያውቀውን ሀቅ ገልብጦ የሚናገር ቀጣፊ ሲያጋጥመው “አይኑን በጨው አጥቦ” በሚል ብሂል ይገልጸዋል። የኢሕዴን/በአዴን ምስለኔወች ግን ፈጽሞ አገር፤ ታሪክ ትውልድ ምን ይለናል ሳይሉ ነው አማራ ሳይሆኑ ባማራነት ስም የጥንት የከዷቸው ጓዶቻቸው የተዋጉለትን እና ጀግኖች የወደቁለትን የወልቃይት፤ የጸገዴ ጸለምት እና እራያን ቆርሰው እና ፈርመው ለህወሓት አሳዳሪወቻቸው ያስረከቡ።
የዛሬ አዲስ ወንበር (ወና ስልጣን) ተረካቢው በአድርባይነትም እንኳን የተሰጠውን “ትልቅ ቦታ” (ለሱ) አመት ሁለት አመት ሳይቆይበት አይገባህም በሚል በአሳዳሪወቹ ሲቀማ ለየትኛው እድሜ እና ሕይወት እንደሆነ ባናውቅም በአማራ ስም ያገኘው ለመሆኑ ግን ጥርጥር የለንም።
ቅራቅንቦ ምስለኔወች ከዳባት እስከ ደብረብርሐን የአማራ ሕዝብን ለማጥፋት ቀን ከሌት ከሰማይ እሳት በምድር ሞርታር እያዘነበ ካለው የኦሮሞ ጽንፈኛ እግር ስር ሲርመጠመጡ የዚህ ትውልድ ወጣት ተርቦች ተሸክሞ የሄደውን መሳሪያ እና ተተኳሽ እያስወለቁ መልሰውታል።ለታየ ሐዝቀስላሴ ቦታ የለቀቀችው እመቤት ሐፍረት የለሽ ምስለኔወችን የበአዴናውያኑ አዋጁን በአማራ ሕዝብ ላይ ያነበቡትን አዋጅ ከሰሙ ማግስት የሽሙጥ ቃላቸውን በማህበራዊ ገጻቸው አስፍረው ነበር መልቀቃቸውን ያበሰሩ።ዘመን ያስቆጠረው ከልጅነት እስከ እዚህ እድሜ የሰውነት ይሉኝታ ያለፈጠረበቱ የሰትየዋን ምሬት እያየ እና እየሰማ ይሁንብኝ ብሎ እጅ ነስቶ ቃለ መሐላ ፈጽሞ ድፍን ኢትዮጵያ ከዶ/ር ነጋሶ እስከ ዛሬ የሚተርትበትን የስልጣን ወና የተረከበው። እንዳማሩ አሞቱ! ዳሩ የባንዳ ምን የክብር ህልፈት አለው?
ታየ ሐዝቀስላሴ ዳላስ ተመላልሶ መጥቷል። በመጣ ቁጥር ግን እኔ እና ለሕዝብ ተቆርቋሪ ወገኖች ባደራጀነው የያኔ የጸረ ወያኔ የውጩ ትግል ቦርሳውን እያስጠቀለልን አባረነዋል። ከሱም ጋር በተለያየ ግዜ የመጡት ምስለኔወች ህላዊ ዮሴፍ፤ ደመቀ መኮነን ወዘተ፤ ተመሳሳይ እድል ነበር የገጠማቸው። እናም በየመጣበት ግዜ ሁሉ ለሕዝብ ስለቆምን ስም እያነሳ ተራ ስድብ ሁሉ ለጥፎብናል ያነን የሚያደርገው ከሆቴል አዳራሾች ሁሉ ሲባረሩ በየግለሰብ ደጋፊወቹ ቤቶች ባደረጉት ስብሰባ የሚናገረውን የምሬት እና አሉባልታ ስድብ እንሰማ ነበር።
በዚህ አድርባይነቱ በየሄደበት የተክቸለቸለው ታየ ከዚህ እድሜ በኋላ በቃኝ ቢል የሚያሳድረው ስራ ባላጣ ነበር ግን ምስለኔው በአማራ ስም ያገኘው ወና ስልጣን አማራ ሆኖ ሳይሆን አማራን የማስፈጀቱ እቅድ አባሪ እና ተባባሪ በመሆን ነበር/ነውም። እንኳን ደስ ያለህ ሳይሆን ቀራቢወቹን እግዜር ያጽና የሚያሰኝ የስልጣን ማማ ብለነዋል!! ያውም ለአረመኔው ስንቶችን አበላሽቶ ከሰውነት ላስወጣው ሰው ያለሆነ ሰው!