October 13, 2024 – Konjit Sitotaw
በደቡብ ሜጫ ገርጨጭ (መሀል ገነት) ከተማ የብልጽግና ሰራዊት የከተማ ነዋሪዎችንና አርሶ አደሮችን ምርኮኛ በሚል ሰብስቦ ዶክመንታሪ በመስራት ላይ ነው ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል።
ወታደራዊ ኮማንዱ አርሶ አደሮችን ከየቤታቸው በመሰብሰብ “ጽንፈኛው ፋኖ አስገድዶ አሰልፎን ነው፣ ፋኖ ዘራፊ ነው” በሉ በሚል በአንድ በኩል አፈሙዝ፣ በአንድ በኩል ካሜራ ተደቅኖ ለዶክመንታሪ ቀረጻ በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል።
ዛሬ ረፋዱን በዚሁ ወረዳ የአብሮ መኖር ገንቦ ማርያም የቅዱስ ዮሐንስ ትምህርት ቤትን በድሮን የመታ ሲሆን፣ ከትናንት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2:00 ድረስ ሙሉ ጦርነት ሲካሄድ ውሏል።
ከአማራ ፋኖ በጎጃም ጋር በተደረገው ከባድ ውጊያ የተመታው ኃይል መሐል ከተማ ላይ የግለሰቦች መኖሪያ ቤት በምሽግነት ሲጠቀም ታይቷል ተብሏል። ዛሬ አርሶ አደሮችንና የከተማዋ ነዋሪዎችን ከየቤታቸው አስገድዶ ሰባስቦ በምርኮ ስም ዶክመንታሪ ሲሰራ ማርፈዱን ተመልክተናል ብለዋል።