October 15, 2024 – Konjit Sitotaw 

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ አገረ ስብከት በ2016 ዓ፣ም 271 የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

በዓመቱ፣ በአገረ ስብከቱ በሽርካ ወረዳ በ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት  91 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ አገረ ስብከቱ መግለጡን ዜና ምንጮቹ ጠቅሰዋል።

በደጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ 150 ምዕመናን፣ በጉሬ ደቢኖ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና አርጆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምዕመናን በተጠቀሰው ዓመት መገደላቸውንና 499 አባወራዎችና እማወራዎች ለስደት መዳረጋቸውን ዘገባዎቹ አውስተዋል።