October 17, 2024 

ጥምረት ለቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ኦርቶዶክሳዊ ንቅናቄ መግለጫ አወጣ!!
++++
የአቋም መግለጫው ማጠቃለያ

** ከፍ ብለን በዝርዝር የጠቀስነውን ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምሥራቅ እስከ ምእራብ በሕዝባችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን መከራ በጥብቅ እናወግዛለን።

** የብልጽግና መንግሥት በዐማርኛ ተናጋሪው ማኅበረ ሰብ ላይ የሚያደርገውን ጦርነትና በንጹሓን ላይ የሚያደርሰውን እልቂትና ፍጅት በጥብቅ እናወግዛለን።

** የብልጽግና መንግሥት በሕዝብ የተጠላ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ተግባር ላይ ያለእንቅልፍ የሚሠራ በመኾኑ በየትኛውም መልኩ ይህንን መንግሥት መታገልና ማስወገድ የኹላችንም ድርሻ በመኾኑ ሕዝቡ እየተደራጀ የሚችለውን ኹሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን።

** ባለ ራእይ አበው የመሠረቱትና አለመታደል ኾኖ ዛሬ በ፵፫ኛ ዓመቱ በራእይ አልባዎች እጅ የወደቀው የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መሪዎችና ተሳታፊዎች ኹላችሁ ዐይናችሁን ከገንዘብና ከሕንጻ ላይ አንሥታችሁ፤ ሐሳባችሁንም ከኅላፊ ምድራዊ ሥልጣንንና ክብር ለይታችሁ መንጋውንና ቤተ ክርስቲያንን ታስቡና ወደ እነሱም በትኩረት ትመለከቱ ዘንድ ፤ ተመልክታችሁም በተአምኖ ኀጣውእ በጸጸት ኾናችሁ እራሳችሁን ከእግዚአብሔር ጋር በማስታረቅ ትውልድንና ሀገርን የሚታደግ የንስሓ ፍሬ የሚገኝበት መንፈሳዊ ጉባኤ እንዲኾን ከእንቅልፋችሁ ትነቁ ዘንድ የመዳን ቀን ዛሬ ነው የሚለውን ቅዱስ ቃል ከማሳሰብ ጋር ይኽን ጉባኤ በመሠረቱትና ዋጋ ከፍለው ለትውልድ ባሸጋገሩት ቀደምት ክዋክብት አበው ስም ታሪካዊ ጥሪ እናቀርብላኋለን።

** የቤተ ክርስቲያን አባቶች እስከ አኹን በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሳችሁት ጥፋት ቀላል አይደለም። ይልቁንም በሕዝብ ላይ የሚደርስን ግፍ ባለመቃወም በዝምታ ማለፍ ከአጥቂው ወገን መሰለፍ መኾኑን እንድታወቁት እያሳሰብን አኹንም ይህንን ግፍ የሚያደርገውን መንግሥት ታወግዙ ዘንድ እንጠይቃለን። https://t.me/AdebabayMedia/3980