October 17, 2024 – Konjit Sitotaw 

ፍሪደም ሃውስ የተባለው ዓለማቀፍ ተቋም ባወጣው መረጃ፣ ኢትዮጵያ በግጭቶችና በመንግሥት ውሳኔ ሳቢያ በአፍሪካ በይነ መረብ ነጻ ያልኾነባት አገር መኾኗን አዲስ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

በጥናቱ ከተካተቱት አገራት መካከል፣ በኢንተርኔት ነጻነት ረገድ ድርጅቱ ከ100ው ለኢትዮጵያ የሰጣት ዝቅተኛው ደረጃ 27 ነው። ሪፖርቱ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ባለሥልጣናት የብሄራዊ ደኅንነትና የጸጥታ ኹኔታዎችን እንደ ምክንያት በመጠቀም የኢንተርኔት ግንኙነቶችን እንደሚያቋርጡና የበይነ መረብ ጋዜጠኞችን እንደሚያሳድዱ የጠቀሰው ሪፖርቱ፣

ይህም ከፍተኛ የኢንተርኔት መብት ገደብ እንዳስከተለ ገልጧል። ይነ መረብ ጋዜጠኞችን ያሳድዳሉ ብሏል።

ጥናቱ የተካሄደው፣ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሱዳንንና ኡጋንዳን ጨምሮ በ17 አገሮች ላይ ነው።