October 17, 2024 – VOA Amharic
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከባድ ዝናባማው አውሎ ነፋስ (ሄሪኬን ሚልተን) አስቀድሞ የታቀደው ጉዟቸውን ለአንድ ሳምንት ከአስተጓጎለው በኋላ ዛሬ ሐሙስ ወደ ጀርመን አቅንተዋል።
ባይደን እና የጀርመኑ መሪ፣ ሁለቱም በቅርቡ ለዩክሬን ይፋ ያደረጉት አዲስ የደህንነት እርዳታ እና የሚሰጡትን ድጋፍ አስመልክቶ ከፍተኛ ጫና እያጋጠማቸው ነው።