October 18, 2024 – Konjit Sitotaw 

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ ሲል በአርሶ አደሮች እንስሳት ላይ ግብር መጣሉን እንደሰማ ጠቅሶ ሸገር ዘግቧል።

የክልሉ መንግሥት አዲሱን ግብር የጣለው፣ የተሻሻለውን ‘’የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር አዋጅ መሠረት በማድረግ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

አዲሱ ግብር የተጣለው፣ አርሶ አደሮች በንብረትነት በያዟቸው የዳልጋ ከብት፣ ጋማ ከብት፣ ፍየል፣ በግ እና ግመል ብዛት ላይ ነው ተብሏል።

የክልሉ መንግሥት ይህንኑ ግብር ለመጣል፣ የአርሶ አደሮችን የቁም እንስሳት መቁጠር እንደጀመረም በዘገባው ተገልጧል።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተቋቋመ ወዲክ፣ በበጀት እጥረት ምክንያት ለመንግሥት ሠራተኞች ሳይቀር ደመወዝ ለመክፈል ተቸግሮ እንደቆየ ይታወቃል።