October 19, 2024 – VOA Amharic
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከኮሬ ዞን 16 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሃይቅ ውስጥ መስመጡን እና 13 ሰዎች እስካኹን የገቡበት አለመታወቁን፣ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ሦስት ሰዎች በህይወት የተገኙ ሲኾን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ እየተፈለጉ እንደኾነ የፖሊስ መምሪያው ሕዝብ ግንኙት ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ ገልፀዋል።