October 19, 2024 – VOA Amharic
ባለፉት ስምት ወራት በአማራ ክልል 66 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መሞታቸውን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ከ4 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ መያዛቸውን ገልጿል።
በተቋሙ የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሞያ ሲስተር ሰፊ ድርብ፤ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ ትላንት ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በ41 ወረዳዎች በተከሰትው የኮሌራ …