እናት ፓርቲ፣ የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላት እንደሆኑ ተጠቅሶ በፓርቲው ከፍተኛ አመራር ላይ ክስ አቀረቡ የተባሉ ግለሰቦች የሄዱበት መንገድ መዋቅሩንና የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ ያልጠበቀ ነው ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በፓርቲው አመራር ላይ ክስና ውንጀላ ካቀረቡት መካከል፣ አንዱ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጥሰት ተገኝቶባቸው ርምጃ የተወሰደባቸውና ከብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚነት የታገዱ እንደሆኑ ፓርቲ ገልጧል፡፡
ፓርቲው፣ ሌላኛው ከሳሽ አገር ውስጥ የሌሉና ካሁን ቀደም የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው ብሏል።
ሆኖም ግለሰቦቹ ባነሷቸው፣ የመዋቅር፣ የመርህ፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የሠራተኛ ቅጥርና የገቢ ምንጭ ጉዳዮች ዙሪያ ፓርቲው ወደፊት ተወያይቶ ዝርዝር ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጧል።
ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት አባላት፣ በፓርቲው ውስጥ ብልሹ አሠራር ሰፍኗል በማለት ምርጫ ቦርድ ጣልቃ እንዲገባ ለቦርዱ የጻፉትን ደብዳቤ መመልከቷን ጠቅሳ ዋዜማ ዘግባ ነበር።