October 22, 2024 – VOA Amharic
በአዲስ አበባ በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ ዛሬ ማምሻውን እሳት መከሰቱ ታውቋል።
“በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል” ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ “የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ” መሆኑን አመልክተዋል።