October 22, 2024 – VOA Amharic
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልንታገለው የሚገባን “የውስጥ ጠላት” አለን የሚለው ንግግር በተቃዋሚዎቻቸው ውስጥ ትልቅ የትችት ማዕበል አስነስቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ የሪፐብሊካን እና የዴሞክራቲክ እጩዎች በምርጫ ዘመቻው ቅስቀሳቸው የሚጠቀሙባቸው የጋሉ ንግግሮች “ዋይት ሀውስን የማሸነፍ ዕድላቸውን ሊጎዳ ይችላል” በሚል የተንታኞችን ማስጠንቀቂያ አስከትሏል፡፡