

ፍሬከናፍር ‹‹በእኔ እምነት ይህ የታደሰው ሕንፃ የአፍሪካን አዲስ ተስፋና አንድነት ያሳያል››
ቀን: October 23, 2024
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ዕድሳት የተደረገለትን የአፍሪካ አዳራሽ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲመረቅ የተናገሩት ኃይለ ቃል፡፡ በዚህ አዳራሽ የተሰባሰቡት አፍሪካውያን ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት – ለአሁኑ አፍሪካ ኅብረት -ሕይወት ለመስጠት እንደነበረ ያስታወሱት የተመድ ዋና ጸሐፊ፣ በአፍሪካ ያለፈ ታሪክና የወደፊት ዕጣ ፈንታ መካከል አዳራሹ እንደ ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግል፣ የጋራ ምኞቶችን እየተቀበለ የጋራ ትግልንና ስኬቶችን እንደሚያከብር አስምረውበታል፡፡ ለአፍሪካና ለዓለም የተሻለ የወደፊት ዕድል ለማምጣት ሁሉም ሰው እንዲተባበር የሚጋብዝ አድርጌ እመለከተዋለሁ ብለዋል።