October 24, 2024 – VOA Amharic
ዋና መቀመጫውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው “ፒፕል ቱ ፒፕል” ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ በምትገኘው የአርሊንግተን ዋና ከተማ የተመሰረተበትን ሃያ አምስተኛ ዓመት መታሰቢያ በማድረግ ዓመታዊ የሕክምና ሳይንስ ጉባኤው አካሂዷል። አብዛኞቹ አባላቱ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሞያዎች ቢሆኑም፤ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የሕክምና ባለ ሞያዎችም ለዓመታት ተሳትፈ…