የመነጣጠጠቅ ባህሪይ ገደል ይዞን እየገባ ነው!
የሸማ ተራ እሳት አደጋ ተጠቂዎች መጽናናቱንና ብርታቱን እንዲሰጣችሁ እመኛለሁ። በአንድ በኩል አደጋ ውስጥ ሆነን ጽናትና ብርታት በሌላ በኩል ደግሞ ሌብነትና ወራዳነት እንዳለ ሁላ ማህበራዊ ጀግንነትም አለ
በፈተናና በውጣ ውረድ ጊዜ የጎደለን መሙላት፣ የደከመን የማበርታትና የመደጋገፍ ባህላችን በከባዱ ተሸርሽሯል ከሚሉት ውስጥ አንዱ ነኝ።
ያልሰራንበትን፣ ያልደከመንበትንና ያላፈራውን ሀብት ከሚመኘው ጀምሮ ገድዬህ ንብረትህን ካልወረስኩ እስከሚለው ድረስ ግለኝነት እንደ አሸን በፈላበት በዚህ ዘመን የኔ ጉዳት ትንሽ ነውና ብዙ የተጎዱ ወንድሞቼ ስላሉ እነሱን እርዱ የሚል ድምጽ ስትሰማ በኩራት ይነዝርሃል።
እጅግ ተስፋ በቆረጥንበት ሰብአዊነትና የሞራል ልዕልና በዘቀጠበት፤ በቁማችሁ እንውረሳችሁ እንዝረፋችሁ የሚሉ በገነገኑበት በዚህ ዘመን ከግለኝነት በላይ የሆኑ ሰዎች ድንገት ብቅ ይሉና ተስፋ ያጭሩብሀል።
ለእንደዚህ ዓይነቱ ምስጉን ተግባር አንዱ ተምሳሌት ሆኖ ያገኘሁት ግለሰብ ትናንት መርካቶ ሸማ ተራ በተከሰተው የእሳት አደጋ ንብረቱ በከፊል ከተጎዱት ውስጥ ” የኔ ጉዳት ከወንድሞቼ ጉዳት አይበልጥምና ድጋፍና እርዳታችሁን ከኔ ይልቅ ለሌሎች አዙሩት ያለው ሐሩን ሰዒድ ነው።
ሐሩን ሰዒድን በግንባር አላቀውም። ተቆርቋሪነቱንና ቀናነቱን የተረዳሁበትን ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ ሲመላለስ አንብቢያለሁ። እንደ ዛሬ አያድርገውና ከራሳቸው ጉዳት የወገናቸው ጉዳት የሚያስቀድሙ በርካታ ሐሩኖች በሀገራችን እንደነበሩ አስታውሳለሁ።
ገንዘብን በፍትሐዊም ሆነ በግፍኝነትና በነውረኛ መንገድ ማጋበስ በማይጠገብበት በዚህ የመጨካከን ዘመን እንደ ሐሩን ዓይነት ማህበራዊ ጀግኖች በስፋት ያስፈልጉናል የሚል እምነት አለኝ።
የፍለጠው፣ ቁረጠው፣ ስቀለውና ዝረፈው (Predatory) የመነጣጠጠቅ ባህሪ ገደል ይዞን እየገባ ነው። እስኪያቅለሸልሸንም አድምጠናል። ይልቅ፣ እኔ ብጎዳም ያንተ ጉዳት ከኔ ጉዳት ይበልጣልና የአንተ መቋቋም የኔ መቋቋም ነው የሚሉ በጋራ ለመለወጥ እንረዳዳ እንደጋገፍን የሚያቀነቅኑ ዜጎችን ሚዲያዎች በስፋት ወደፊት እንድታመጡ እጠይቃለሁ።
ያልሰራንበትን፣ ያልደከመንበትንና ያላፈራውን ሀብት ከሚመኘው ጀምሮ ገድዬህ ንብረትህን ካልወረስኩ እስከሚለው ድረስ ግለኝነት እንደ አሸን በፈላበት ዘመን የኔ ጉዳት ትንሽ ነውና ብዙ የተጎዱ ወንድሞቼ እርዱ የሚል ድምጽ መስማት ይነዝርሃል።
እጅግ ተስፋ በቆረጥንበት ሰብአዊነትና የሞራል ልዕልና በዘቀጠበት፤ በቁማችሁ እንውረሳችሁ እንዝረፋችሁ የሚሉ በገነገኑበት በዚህ ዘመን ከእልፎች መሐል አንዳንድ ሰዎች ብቅ ድንገት ብቅ ይሉና ተስፋ ያጭሩብሀል።
ለእንደዚህ ዓይነቱ ምስጉን ተግባር አንዱ ተምሳሌት ሆኖ ያገኘሁት ግለሰብ ትናንት መርካቶ ሸማ ተራ በተከሰተው የእሳት አደጋ ንብረቱ በከፊል ከተጎዱት ውስጥ ” የኔ ጉዳት ከወንድሞቼ ጉዳት አይበልጥምና ድጋፍና እርዳታችሁን ከኔ ይልቅ ለሌሎች አዙሩት ያለው ሐሩን ሰዒድ ነው።
ሐሩን ሰዒድን በግንባር አላቀውም። ነገር ግን ተቆርቋሪነቱንና ቀንነቱን የተረዳሁበትን ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ ሲመላለስ አንብቢያለሁ። እንደ ዛሬ አያድርገውና ከራሳቸው ጉዳት የወገናቸው ጉዳት ይበልጥ የሚያስቀድሙ በርካታ ሐሩኖች በሀገራችን እንደነበሩ አስታውሳለሁ።
ገንዘብን በፍትሐዊም ሆነ በግፍኝነትና በነውረኛ መንገድ ማጋበስ በማይጠገብበት በዚህ የመጨካከን ዘመን እንደ ሐሩን ዓይነት ማህበራዊ ጀግኖች በስፋት ያስፈልጉናል የሚል እምነት አለኝ።
የፍለጠው፣ ቁረጠው፣ ስቀለውና ዝረፈው (Predatory) የመነጣጠጠቅ ባህሪይ ገደል ይዞን እየገባ ነው። እስኪያቅለሸልሸንም በየ ማዳያው እያዳመጥነው ነው። ይልቅ፣ እኔ ብጎዳም ያንተ ጉዳት ከኔ ጉዳት ይበልጣልና የአንተ መቋቋም የኔ መቋቋም ነው የሚሉ በጋራ ለመለወጥ እንረዳዳ እንደጋገፍን የሚያቀነቅኑ ዜጎችን ወደ ሚዲያዎች በስፋት ወደፊት እንዲያመጡ እንድናበረታታ እጠይቃለሁ።
ሙሼ ሰሙ