ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በውጭ ሀገራት ለመገናኘት ሀሳብ ማቅረቡን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ
የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንዳሉት የታጠቁ ኃይሎች እና ራሳቸውን ከምክክሩ ያገለሉ ፓርቲዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
“የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም ያሉት ኮሚሽነሩ የፖለቲካ ጥያቄ አቅርበው በምክክሩ እንዲሳተፉ በተለያየ መንገድ ጥሪ አድርገናል፤ ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል ሲሉ ከዚህ በፊት የተደረገውን ጥረት አንስተዋል።
ከግጭት እና ጦርነት ያተረፍነው እንግልትና ስቃይ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን እኛ የማደራደር ሀላፊነት ባይኖረንም ግጭቶች የሚፈቱበትን መንገድ የመቀየስ ስራ ግን እንሰራለን ብለዋል፡፡