October 25, 2024 – Konjit Sitotaw 

በነሽመል አብዲሳ መመሪያ ኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ፣ ወዴሳ ወረዳ፣ ኮዬ ፈቼ ክ/ከተማ በደረሰኝ የተደገፈ በኑሮ ውድነት ላይ ሌላ ውድነትንና እሮሮ የሚጨምር የግዴታ መዋጮ ዝርዝር፣

ለስፖርት ምክር ቤት 250.00
ለሚሊሻ ድጋፍ         600.00
ለቡሳ ጎኖፋ           1,000.00
ምክንያቱ ያልታወቀ 1,000.00
ለጣራና ግርግዳ  10,715.85 (ለባለ 2 መኝታ ነው)
==================================
ጠቅላላ              13,565,85

የሚገርመው ነገር ክልሉ መኖሪያ ቤቶቹን ከአዲስ አበባ ከተማ ከተረከባቸው አምስት አመት ያለፈውና ከተማውን ምሳሌ የሚሆን Smart City አደርገዋለሁ ብሎ በየሚዲያው ያሳወጀ  ቢሆንም በሰፈሩ ውኃ፣ መብራት፣ መንገድና የትራንስፖርት አቅርቦት ጨርሶ የለም።

ሌላውና አሳፋሪው ነገር አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለ2 መኝታ ቤቶች የጣራና ግርግዳ ክፍያቸው ከ3,500 ብር በታች ሆኖ እያለ የሸገር ሲቲው ግን ከ3 እጥፍ በላይ መሆኑ ነው።

አገሪቱ ሃይ ባይ ማጣቷ እጅግ አሳዛኝ ነው።

የኗሪዎች ኡኡታ!!!!