October 25, 2024 – Konjit Sitotaw 

“በመንግሥት በኩል አስክሬናቸውን የመፈለግ ሥራ ቆሟል”  -የክልሉ ኮምዩኒኬሽን

በጋምቤላ ክልል መስከረም 15/2017 ዓም  ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ በጂካዎ ወረዳ የባሮ ወንዝ ጊዜያዊ ድልድይን ጥሶ በወንዝ ውስጥ በመግባቱ 7 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ገልጾ ነበር።

አደጋው ካጋጠመ በኋላ በተደረገ ፍለጋ የአንድ ሰው አስክሬን ማግኘት ቢቻልም ሲጓጓዙበት የነበረውን አምቡላንስ ጨምሮ ቀሪ ስድስት አስክሬኖች እስካሁን አልተገኙም።

በዛሬው ዕለት አንድ ወር የሆነው ይህ አደጋ አስክሬናቸውን የመፈለጉ ሥራ በመንግስት በኩል መቆሙን የክልሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ የሆኑት አቶ ኦጁሉ ጊሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ከሟቾች መካከል በክልሉ ኑዌር ዞን የሚገኘው ኒን ያንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኞች የሆኑት 7 ሰዎች ነበሩበት።

በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች የዓይነት ድጋፍ መደረጉን ያነሱት ባለሞያው አስክሬናቸውን የመፈለግ ሥራው ግን የባሮ ሃይቅ እስካሁን ባለመጉደሉ እና በከፍተኛ ፍጥነት የሚምዘገዘግ በመሆኑ የአምቡላንሱንም ሆነ የአስክሬናቸውን አቅጣጫ ይለውጣል “አይገኝም” ነው ያለት።

የባሮ ወንዝ የሚቀንስበት ወቅት ከህዳር በኋላ ነው ያሉት አቶ ኦጁሉ አሁን ባለበት ሁኔታ ግን ምንም መቀነሱን የሚያሳይ ምልክት የለም ሲሉ ነው የገለጹት።