October 29, 2024 

” ሲሾሙ ‘ ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ‘  ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉና እንዳላደረጉ አይነገረንም ” – ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ደሳለም ጫኔ (ዶ/ር) ከሚሰጡ ሹመቶች ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥያቄ በምክር ቤት አንስተዋል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፥ ” የሚነሱ ሚኒስትሮች ከሾናቸው በኃላ ምን አጉለው እንደተነሱ ፤ ምን ድክመት እንዳሳዩ ፤ ወይ ምን የስነምግባር ጥሰት እንዳሳዩ አይቀርብም ፤ በተጨማሪም እነሱን የሚታኳቸው ሚኒስትሮች ከነሱ በምን እንደሚሻሉ አይነገረም ” ብለዋል።

” እርግጥ ሲሾሙ ‘ ወጣት ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ጥሩ ‘ ምናም ተብሎ ይሾማል ሲወርዱ ግን በምን ፐርፎርም እንዳደረጉ በምን ፐርፎርም እንዳላደረጉ አነገረንም። ” ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት መርህ አንጻር ጥያቄ እየሚያስነሳ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ሚኒስትሮች ከቦታቸው ሲወርዱ ለምን በምን ምክንያት እንደወረዱ ፤ በምትካቸው የሚመጡትም ከነሱ በምን እንደሚሻሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ ምክር ቤቱም ማወቅ የለበትም ? ሲሉ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጠይቀዋል።