October 30, 2024 – VOA Amharic
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) እና አጋር በሆኑ የአረብ ሚሊሻዎች ከ18 ወራት በላይ በዘለቀው ጦርነት ከስምንት እስከ 75 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ “ዘግናኝ” የሆነ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልእኮ ዘገባ አመልክቷል።
ዛሬ ማክሰኞ የወጣው የመንግሥታቱ ድርጅት ተልእኮ ዘገባ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎቹና አጋሮቹ ሰለማዊ ዜጎችን በመድ…