October 30, 2024 – Konjit Sitotaw
የሱማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ፣ ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞና ጫና ቢደርስባት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ለቢቢሲ ሱማሌኛ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ቢሂ፣ በሶማሌላንድና ግብጽ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ግብጽ እንድትገባበት መደረጉን ጠቅሰው፣ የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሶማሌላንድ ራሷን የቻለች አገር መኾኗን ከተቀበሉ ንግግር ማድረግ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንቱ፣ የሱማሊያና ግብጽ ወታደራዊ ስምምነት የሶማሌላንድን የሉዓላዊ አገርነት ሂደት ለማስቆም ያለመ ነው በማለት ከሰዋል።
ባንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ ይኾናል የተባለው የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን ተግባራዊ ላለመኾኑ፣ የሱማሊያ ተቃውሞ አስተዋጽኦ እንደሌለውም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።