

ፍሬከናፍር ‹‹ኢትዮጵያ በታሪኳ የትብብር ከፍ ሲልም ለሌላው የመትረፍ ልምድ ያላት አገር ናት››
ቀን: October 30, 2024
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ 117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲከበር የተናገሩት፡፡ ኢትዮጵያ ትብብርና መግባባትን መርሆዋ አድርጋ ከጎረቤት አገሮች ጋር ግንኙነቷን እንደምትቀጥል የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ከመተባበር ውጪ ደግሞ ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳን በውይይትና በመግባባት እንዲፈታ የምትፈልግ የመርህ አገር ናት ሲሉ ገልጸዋል:: ለምክክር ዝግጁ መሆን አስፈላጊ ቢሆንም የአገሪቱ የፖለቲካ ነፃነትና ሉዓላዊነት የሚበየነው በጀግናው ሠራዊት ተጋድሎ ነው ሲሉ አመልክተዋል::