ፋሲል የኔአለም እንደፃፈው …….. ጠ/ሚ አብይ አህመድ በአፄ ኃይለስላሴ ዘመን ተቆልፎበት የነበረ 4 ኩንታል ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ማስገባታቸውን ተናግረዋል። ይህን የወርቅ ክምችት ከእርሳቸዉ በፊት የነበሩ መንግሥታት ሳያገኙት፣ እርሳቸው እንዳገኙት ተናግረዋል።
ደርግ ንጉሱን የደበቁትን ወርቅ አምጡ እያለ ሲያሰቃያቸው፣ ስለዚህ ወርቅ ምንም አያውቅም ነበር ማለት አይቻልም። ኢህዴግም በተመሳሳይ አያውቅም ነበር ብሎ ለመናገር ከባድ ነው።
የሚመስለኝ ሁለቱም መንግሥታት የሚዘረፈውን ወርቅ ዘርፈው፣ ይህን ወርቅ የተውት ፣ ወርቁ በ ጥፍጥፍነት ( bullion ) መልክ ሳይሆን በቅርሳቅርስ ስለተቀመጠ ነው። የወርቅ ቅርሶችም በስጦታ መልክ ከተለያዩ አገራት የተበረከቱ ናቸው ብዬ እገምታለሁ።
አብይ ወደ ባንክ አስገባሁት የሚለው ቅርሶችን ከሆነ ትልቅ ወንጀል ነው። ምክንያቱ ቅርሶች ቀልጠው ወደ ጥፍጥፍ ወርቅ የሚቀየሩበት እድል ሰፊ ስለሚሆን ነው። ቅርስ ብሄራዊ ሙዚየም እንጅ ብሃራዊ ባንክ አይገባም።
ምንአልባትም አንዳንድ ውድ ቅርሶች ወጥተው ተሸጠው ይሆናል። ለአብይ ቤተ መንግሥት የማሰሪያው ገንዘብም ከማህበራዊ ፈንድ ተቋም ከሚወሰደው በተጨማሪ፣ ከማይታወቁ ቅርሶች ሽያጭ የተገኘም ሊሆን ይችላል። (በነገራችን ላይ የዩናይትድ አረብ ኢሚሬትሱን መሪ አላምነውም። )
ይህ ጉዳይ ገለልተኛ በሆነ አጣሪ ኮሚቴ ሊመረመር እና ይፋ ሊሆን ይገባዋል። የተገኘው ቅርስ ነው ወይሰ ጥፍጥፍ ወርቅ የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት። በቅርፃቅርፅነት የተቀመጠ ወርቅ ከሆነ፣ ወደ ብሄራዊ ባንክ የገባው፣ ባንኩ እንዳይነካው መታገድ አለበት።
ህዝብ ከአንድ ፣ ያውም የመታመን እድሉ ካሽቆለቆለ ፖለቲከኛ የሚነገረውን ሁሉ አምኖ መቀበል የለበትም።
( በነገራችን ላይ ከ 3 ወር በፊት IMF ንግድ ባንክን ከመፍረስ አዳነው በዬ ስፅፍ፣ ካድሬው ሁሉ ውሸት፣ ንግድ ባንክ 25 ቢሊዮን ብር አትርፏል እያሉ ማስረጃ አምጣ እያሉ ሲጮሁብኝ ነበር። እነሆ ዋናው ሰው ዛሬ አፈረጠው። ካድሬው ግን አይገባውም፣ ቢገባውማ ጭፍን ካድሬ ባልሆነ ነበር።)
Fasil Yenealem