አካባቢውን እየረበሸ ያለው የባዶ ቅል ጥሬ መንኳኳት!
የባዶ ቅል ጥሬ መንኳኳት አካባቢውን እየረበሸው እንደኾነ ወዳጆቻችን ነግራችኹናል። በርግጥ ሲታዘብ ለኖረ ተከታታይ ይህ የባዶው ቅል ጥሬ መንኳኳት አዲስ ነገር አይደለም። የባዶው ቅል ጥሬ መንኳኳት የጀመረው ገና የፋሽስት ወያኔን ጠረን እንደያዘና የኢሕአዴግን ቆብ ባግባቡ ሳያወልቅ “ዳያስፖራ” በሆነ በማግስቱ ነበር።
የሚንኳኳው የባዶ ቅል ጥሬ ራሱን ለግንቦት ሰባት ለመሸጥ ሲል “ሬድዋን ሁሴን ደሞዝ የሚከፍላቸው የአማራ ተጋድሎ እያሉ የሚጮሁ አሉ”፤ “አማራ አማራ የሚሉ ወያኔዎች በዲያስፖራ አሉ” እያለ የአማራን ሕዝባዊ ተጋድሎ ማራከስ ውስጥ የገባው፤ መጽሐፍ ጻፍኹ ብሎ በወያኔ ቤት በተካነበት ካድሬያዊ “ጥበብ” አማራን በጎጥ መከፋፈል የጀመረው በባሕር ማዶ የወራት ያህል የጥሞና ጊዜ ሳይኖረው ነበር።
ምን ይኼ ብቻ! በጃዋር ቴሌቭዥንም ቀርቦ የኦነግ የሃይማኖት ክንፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹን እነ አሕመዲን ጀበልን ልዕለ ሰብዕ አድርጎ ከሰቀለ በኋላ “ኦሮሞ ከደረሰበት በደል ብዛት የተነሳ ልገንጠል ቢል እንኳን ትግሉን እደግፋለኹ” እያለ አንድ ጥሬ እንደያዘችው ቅል በቂ ትምህርትና ዕውቀት ሳይኖረው በምላሱ ኃይል ብቻ ከፍተኛ ስሜታዊ ጩኸትና ቅጥፈታዊ መንኳኳትን የማወናበድ ስራው አድርጎ የያዘው “በዳያስፖራነት” ውሎ ሳያድር ነበር።
ይህ የባዶ ቅል ጥሬ ከሰሞኑ ማይምነትና ድንቁርና በሰጠው ድፍረቱ እየተመካ የእውቀት ጠብታ በውስጡ ሳይኖረው በማይደርቀው የእውቀት ባሕር ላይ የስድብ አፉን ከፍቷል። ይህ የሚንኳኳ የባዶ ቅል ጥሬ እውቀት ማለት የወያኔ አጋዘን፤ የግንቦት ሰባት አጋሰስና የኦነግ ከብት መሆን ሳይመስለው አልቀረም።
በርግጥ የሚንኳኳው የባዶ ቅል ጥሬ ዋናው ባለጉዳዩ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሲል ከተነገረው ጉዳይ ጋር የማይገናኝ መንጠላጠያ ፈጥሮ እንካችሁ ያለውን ውንጀላ ማስተጋባቱ የወያኔ አጋዘን በነበረበት ወቅት “ማወቅ ማለት ሲባል የሰማውን መድገም ነው” የሚባለው ካድሬያዊ ስልጠናው ውጤት ቢሆንም ቅሉ የተነሳው የባንዶች የተጠያቂነት ጉዳይ ግን “የገብርኤልን መገበሪያ የበላ ያስለፈልፈዋል” እንደሚባለው አሰላለፉን እያስተካከለ ሲገለባበጥ በኖረበቱ የትናንት ሕይዎቱ የሰራው አዳፋ ተግባሩን በመስታዎት እያዬ ያልታረመ አፉን አስከፍቶ ቢያስለፈልፈው የማይጠበቅ አይደለም።
ባጭሩ በራሳቸው ጥረት በባዕድ ቋንቋ የተጻፉ ዋና ቅጂዎችን ሳይቀር ከያሉበት አፈላልገው ራሳቸውን የውጭ ቋንቋ ጭምር በማስተማር አማራ ጠሎች በፈጠራ ታሪክ ላይ ተመስርተው ሲያዛቡት የከረሙትን ታሪካችንን በማቃናትና ትክክለኛውን መስመር በማስያዝ፤ ምርቱንና ግርዱን በመለየት እውነተኛው ጉዳይ ተገላልጦ እንዲወጣ ጤናቸውውን ጭምር አጥተው ለከፈሉት የጊዜና የአእምሮ ድካም እጅግ ከፍ ያለ ምስጋና በሚገባቸው የእውቀት አድባሮች ላይ በቂ ትምህርትና ሙያ የሌለው የባዶ ቅል ጥሬ ጩኸታም የሚያሰማው ኳኳታ ዝም ተብሎ ከማይታለፍበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
በድምጽ፣ በተንቀሳቃሽ ምስልና በጽሑፉ የከዘንነው የወያኔ አጋዘንነቱ፣ የግንቦት ሰባት አጋሰስነቱና የኦነግ ከብትነቱ ታሪክ ጊዜውን እየጠበቀ እንጂ ተረስቶ አልነበረምና ዝም የተባለው በትዕግሥት ይጠብቅ።