ካማላ ሃሪስዴሞክራት
ዶናልድ ትራምፕሪፐብሊካን
ለማሸነፍ የሚያስፈልገው 270
223 279
66,443,509 ድምጽ(47.4%)
71,491,756 ድምጽ(51%)
ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲመረጡ ፣ ሪፐብሊካኖች በሁለቱም ምክር ቤቶች የበላይነት እየያዙ ነው

ከ 7 ሰአት በፊት
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸውን አሳይቷል።
ትራምፕ ወሳኝ የሆኑትን ግዛቶች ላይ የበላይነት በማግኘት የዲሞክራቶቹ ዕጩ ካማላ ሃሪስን በሰፊ ልዩነት በመምራት ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን የ270 ኤሌክቶራል ድምጽ አግኝተዋል።
ሪፐብሊካኖች ድላቸውን ይፋ ለማድረግ ሽር ጉድ እያሉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕም የአሸናፊነታቸውን ንግግር አድርገዋል።

አሜሪካውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ከሰጡት ድምጽ በተጨማሪ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት (ሴኔት) እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ኮንግረስ) አባልነት ለሚወከሉ ሰዎች ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
በዚህም መሠረት በሴኔቱ ውስጥ ሪፐብሊካኖች የበላይነትን ለማግኘት ችለዋል። ባለፉት አራት ዓመታት በዲሞክራቶች የበላይነት ተይዞ የነበረው የሕግ መሰኛው ምክር ቤት አሁን ሪፐብሊካኖች አብላጫውን እንዳገኙበት የወጣው ውጤት ያሳያል።https://flo.uri.sh/visualisation/20078266/embed?auto=1
እስካሁን በታወቁት የምርጫ ውጤቶች እና በሂደቱ ላይ በመመሥረት በተሰጡ ግምቶች ሪፐብሊካኖች ድል እየቀናቸው ይመስላል። ትራምፕ ፕሬዝዳንት ለመሆን ጥቂት ኤሌክቶራል ድምጽ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ ካማላ ወደ ኋላ ቀርተዋል።
በኮንግረሱ ውስጥም ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች የበለጠ መቀመጫ አግኝተዋል። ይህ መጪዎቹ አራት ዓመታት በአሜሪካ ሁለቱም ምክር ቤቶች ውስጥ ሪፐብሊካኖች የበላይነት መያዛቸው ዕውን እየሆነ ይመስላል።https://flo.uri.sh/visualisation/20078381/embed?auto=1