- ቀጥታ,ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
- የሪፐብሊካኑ ዕጬ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ከስምንት ዓመት በፊት ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ምርጫን አሸንፈው አገሪቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት ለመምራት ወደ ዋይት ሃውስ ይመለሳሉ። የ78 ዓመቱ ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” ሲሉ ተናግረዋል። ቢቢሲ አማርኛ የአሜሪካ ምርጫ ሂደትን የተመለከቱ ዘገባዎች በዚህ ገጽ በቀጥታ ያቀርባል።
የሪፐብሊካኑ ዕጬ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ከስምንት ዓመት በፊት ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ምርጫን አሸንፈው አገሪቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት ለመምራት ወደ ዋይት ሃውስ ይመለሳሉ። የ78 ዓመቱ ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” ሲሉ ተናግረዋል። ቢቢሲ አማርኛ የአሜሪካ ምርጫ ሂደትን የተመለከቱ ዘገባዎች በዚህ ገጽ በቀጥታ ያቀርባል።
ጭምቅ ሃሳብ
- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለትራምፕ ‘የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት’ አስተላለፉ
- ትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” አሉ
- ትራምፕ ፕሬዝዳንት ለመሆን ሲቃረቡ፣ ሪፐብሊካኖች በሁለቱም ምክር ቤቶች የበላይነት እየያዙ ነው
- ሪፐብሊካኖች የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይቆጣጠራሉ- ትንበያ
- የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው
- ትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛትን አሸነፉ
- የአሜሪካዊ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤት እንደ ሩሲያ እና ቻይና ላሉ ኃያላን ሀገራት ምን ይፈይዳል?
- የፕሬዚዳንታዊ እጩዎቹ የምርጫ ዘመቻ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው?
- የአይዋ ግዛት ለምን የትኩረት ማዕከል ሆነች?
- “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” ካማላ ሃሪስ
- ከምርጫው ቀን በፊት ከ70 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ሰጥቷል
- እስካሁን ባለው ሂደት ከ78 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን ይህም ከአራት ዓመት በፊት የነበረውን የመጀመሪያ መራጮች ተሳትፎ ክብረ ወሰን የሰበረ ነው
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊት“የአሜሪካ 47ኛ እና 45ኛ ፕሬዝዳንት እንድሆን ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ”Play video, ““የአሜሪካ 47ኛ እና 45ኛ ፕሬዝዳንት እንድሆን ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ””, ርዝመት 0,3900:39
የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,“የአሜሪካ 47ኛ እና 45ኛ ፕሬዝዳንት እንድሆን ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ”45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋይት ሐውስ በጆ ባይደን ተሸንፈው ከተሰናበቱ ከአራት ዓመታት በኋላ 47ኛው ፕሬዝዳንት ለመሆን ተመርጠው በመጪው ጥር ወደ ዋይት ሐውስ ይመለሳሉ። ለዚህም አሜሪካውያንን አመስግንው ያለዕረፍት እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል።ያጋሩ, “የአሜሪካ 47ኛ እና 45ኛ ፕሬዝዳንት እንድሆን ስለመረጣችሁኝ አመሰግናለሁ”
- ከ 2 ሰአት በፊትበአሜሪካ ታሪክ ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ በድጋሚ የተመረጡ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ዶናልድ ትራምፕ ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ከሚሆኑት ጄ ዲ ቫንስ ጋርታሪካዊ በሆነው ምርጫ ወደ ሥልጣን ለመመለስ የሚያስችላቸውን የበላይነት ያገኙት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ዋይት ሐውስ ሊመለሱ ነው።እስካሁን በተገኘው ውጤት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ሥልጣንን መልሶ ለመያዝ ከሚያስችላቸው 270 የግዛቶች ድምጽ ከ279 በላይ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል።ትራምፕ ከአራት ዓመታት በፊት በጆ ባይደን ከተሸነፉ በኋላ በከባድ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ገብተው ነበር።ደጋፊዎቻቸው የአገሪቱን ምክር ቤት እንዲወሩ አድርገው ተጭበርብሯል ያሉትን የምርጫ ውጤት በኃይል ለመቀልበስ ሞክረዋል በመባላቸው የፖለቲካዊ ሕይወታቸው ፍጻሜ ይሆናል ተብሎ ነበር።በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በተለይም በመዋሸት እና በማጭበርበር ከ90 በላይ ተደራራቢ ክሶች ቀርቦባቸው ለዓመታት ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩ ሲሆን፣ አሁንም ክሳቸው ዕልባት አላገኘም።በተጨማሪም በዘመናዊ የአሜሪካ የፕሬዝዳንቶች ታሪክ ውስጥ ሁሉም ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን የተመረጡት የመጀመሪያውን የፕሬዝዳንትነት ጊዜያቸውን ተከትሎ ነበር።በዚህም ሳቢያ ትራምፕ ዋይት ሐውስን ከለቀቁ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ መወዳደራቸው ውጤት አያስገኝላቸውም ተብሎ ነበር። ነገር ግን በአሜሪካ የፕሬዝዳንትነት ታሪክ በተለያየ ጊዜ በድጋሚ የተመረጡ ሁለተኛው ሰው ሆነዋል።በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከታታይ ባልሆነ የሥልጣን ዘመን በሌላ ዙር ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው ወደ ሥልጣን የመጡት የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ግሮቨር ክሌቭላንድ ናቸው።ፕሬዝዳንት ክሌቭላንድ በአውሮፓውያኑ ከ1885 እስከ 1889 በሥልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ በቀጣዩ ምርጫ ተሸንፈው፤ ከአራት ዓመታት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በመወዳደር ተመርጠው ከ1893 እና 1897 ድረስ በድጋሚ አገልግለዋል።ያጋሩ, በአሜሪካ ታሪክ ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ በድጋሚ የተመረጡ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት
- ከ 3 ሰአት በፊትየትኞቹ ግዛቶች ወሳኙን ድምጽ ለትራምፕ ሰጡ?ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት በመሆን አሸናፊ ሆነዋል። በአገሪቱ የምርጫ ታሪክ ከባድ ፉክክር በተደረገበት እና አሸናፊውን ቀድሞ ለመለየት አዳጋች በነበረው በዚህ ምርጫ ትራምፕ ከፍተኛውን የግዛቶች የምርጫ ድምጽ አግኝተው አሸናፊ ሆነዋል። ገና ውጤታቸው ሙሉ ለሙሉ ያልታወቁ ግዛቶች ቢኖሩም አሁን ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ተለይተዋል። የትኞቹ የአሜሪካ ግዛቶች ያላቸውን ወሳኝ ድምጽ ለማን ሰጡ?
ያጋሩ, የትኞቹ ግዛቶች ወሳኙን ድምጽ ለትራምፕ ሰጡ?
- ከ 3 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
የፎቶው ባለመብት,Reutersሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ከስምንት ዓመት በፊት ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ምርጫውን አሸንፈው አሜሪካን ለቀጣይ አራት ዓመታት ለመምራት ወደ ዋይት ሃውስ ይመለሳሉ።የ78 ዓመቱ ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” ሲሉ ድላቸውን ቀድመው አብስረዋል።አክለውም “ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል” ሲሉም የምርጫ ዘመቻ መፈክራቸውን በመጠቀም ተናግረዋል።ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫው ወሳኝ በሚባሉት ሰሜን ካሮላይና፣ ዊስኮንሰን፣ ፔንስልቬንያ እና ጆርጂያ ግዛቶችን ማሸነፋቸውን ተከትሎ 47ኛ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ያረጋገጡት።ትራምፕ ከሚያስፈልጋቸው 270 ኢሌክቶሪያል ኮሌጅ ውስጥ 279 በማግኘት አሸንፈዋል።የዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ ሽንፈታቸውን አስመልክቶ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ያልተነጋገሩ ሲሆን የመጨረሻው ውጤት ይፋ ከመሆኑ በፊት ነበር ደጋፊዎቻቸው የመመልከቻ ማዕከሏ ስፍራን ለቀው የሄዱት።በተጨማሪም ሪፐብሊካኖች የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔትን) አብላጫ ድምጽ በመያዝ የዲሞክራቶችን የበላይነት ወስደዋል።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
- ከ 4 ሰአት በፊትየአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው? ድምፅ የሚቆጠረውስ እንዴት ነው?
አሜሪካዊያን ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ወደ ምርጫ ጣቢያዎች አምርተው ለፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።እርግጥ ነው በዩናይትድ ስቴትስ ሰዓት አቆጣጠር መሠረት ድምጽ መስጠቱ በአብዛኞቹ ግዛቶች ማክሰኞ ከሰዓት አካባቢ ተጀምሮ ረቡዕ ማለዳ ተጠናቋል።የድምፅ መስጫው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላም አሸናፊው ወይም አሸናፊዋ ለሰዓታት ላይታወቁ ይችላሉ። ሰዓታት ብቻ አይደለም፤ ቀናት አሊያም ሳምንታት ሊወስድ ይችላል።በአሁኑ ምርጫ ግን ረቡዕ ረፋድ ላይ ዶናልድ ትራምፕ አብላጫውን በመያዝ በሰፊ ልዩነት ካማላ ሃሪስን በመምራታቸው አሸናፊነታቸው ዕውን እየሆነ ነው።እነሆ ስለምርጫው ውጤት ሊያውቋቸው የሚገቡ አንዳንድ ጉዳዮችን እዚህ በዝርዝር ይመልከቱ የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው? ድምፅ የሚቆጠረውስ እንዴት ነው?ያጋሩ, የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው? ድምፅ የሚቆጠረውስ እንዴት ነው?
- ከ 5 ሰአት በፊትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ለትራምፕ እንኳን ደስ አለዎት አሉ
የፎቶው ባለመብት,PM officeየአሜሪካ የምርጫ ውጤት በይፋ ባይገለጽም የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ ድል አድርጌያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላለፉ።በምርጫዎ ድልዎት እና ወደ ስልጠን በመለለስዎ እንኳን ደስ አለዎት ማለት እፈልጋለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።አክለውም “በእርስዎ የስልጣን ዘመን የሁለቱን አገራት ግንኙነት በበለጠ ለማጠናከር በጋራ የምንሰራበትን ጊዜ እጠብቃለሁ” ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ለትራምፕ እንኳን ደስ አለዎት አሉ
- ከ 5 ሰአት በፊትትራምፕ ለአሜሪካ ከፈጣሪ የተላኩ መሪ ናቸው ብለው የሚያምኑት ቀኝ ዘመም ክርስቲያኖች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ትራምፕ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ሲጸልዩበድሃ ማኅበረሰቦች ውስጥ ትናንሽ አብያተ ክርስቲያናትን በማቋቋም፣ በባይብል ቤልት ውስጥ ያሉ ፓስተሮች በአማኞች መካከል ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ብዙዎቹንም ወደ ሪፐብሊካን ፓርቲ ወግ አጥባቂ መስመር ይመራሉ።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ትራምፕ ለዚህ ቡድን ምርጥ መዘወሪያ ሆነዋል።የኦክላሆማው ፓስተር ጃክሰን ላህሜየር የትራምፕ ታማኝ ደጋፊ ናቸው።“ፓስተርስ ፎር ትራምፕ” [ትራምፕን የሚደግፉ ፓስተሮች] የተሰኘው ቡድን መሥራች የሆኑት ላህሜየር “ይህችን አገር እንዲያስተዳድር ትራምፕ በእግዚአብሔር ተልኳል” ብለዋል።ዓላማቸውም በሚቀጥለው ምርጫ ትራምፕን ለመደገፍ “የወንጌላዊውንን ድምጽ ማሰባሰብ” ነው።በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከግድያ ሙከራ መትረፋቸውን “መለኮታዊ ተአምር ነው” በማለት ላህሜየር ጠርተውታል።የቀድሞ የሴኔት ዕጩ ተወዳዳሪ በስልክ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “አገራችን ለእርስ በርስ ጦርነት አንድ እርምጃ ቀርቷታል” ብለዋል።የፕሮቴስታንት ፓስተሮቹ እና የፖለቲካ አክቲቪስቶቹ እንደ ክርስቲያን ብሔርተኛ ለመቆጠር ፈቃደኛ አልሆኑም።“ይህ መገናኛ ብዙኃን እኛን ለዲሞክራሲ ስጋት አድርገው ለመሳል በላያችን ላይ የጫኑት ስም ብቻ ነው። እውነት ግን አይደለም” ብለዋል። ሙሉውን እዚህ ያንብቡ ትራምፕ ለአሜሪካ ከፈጣሪ የተላኩ መሪ ናቸው ብለው የሚያምኑት ቀኝ ዘመም ክርስቲያኖችያጋሩ, ትራምፕ ለአሜሪካ ከፈጣሪ የተላኩ መሪ ናቸው ብለው የሚያምኑት ቀኝ ዘመም ክርስቲያኖች
- ከ 6 ሰአት በፊትየአነጋጋሪው ዶናልድ ትራምፕ የሕይወት ታሪክ – ከሪል ስቴት እስከ ፖለቲካ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesዶናልድት ሦስት ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ሙከራ ከማድረጋቸው በፊት በአሜሪካ ታዋቂ እና አነጋጋሪ ቢሊየነር ነበሩ።ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን የተወዳደሩት በአውሮፓውያኑ 2016 ነው። ነገር ግን በኒው ዮርክ ግዙፍ የሪል ስቴት ኩባንያ ባለቤት የሆኑትን ባለሀብት ከዚያም በፊትም የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ትኩረት ነፍገዋቸው አያውቁም።ስማቸው ገናና መሆኑ እና ከዚህ ቀደም ለየት ባለ መልኩ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ጉምቱ ፖለቲከኞችን በመርታት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ሳያደርጋቸው አልቀረም። ቢሆንም አነጋጋሪው ፕሬዝደንት ከአራት ዓመታት በኋላ በምርጫ ተሸንፈው ከሥልጣን ተወግደዋል።ሥልጣን የለቀቁበትን ሽንፈታቸውን አሁን ድረስ በፀጋ ያልተቀበሉት የ78 ዓመቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ትራምፕ ድጋሚ መንበረ-ፕሬዝደንቱን ለመቆጣጠር በቅተዋል። ሙሉውን ታሪክ እዚህ አንብቡ የአነጋጋሪው ዶናልድ ትራምፕ የሕይወት ታሪክ – ከሪል ስቴት እስከ ፖለቲካያጋሩ, የአነጋጋሪው ዶናልድ ትራምፕ የሕይወት ታሪክ – ከሪል ስቴት እስከ ፖለቲካ
- ከ 6 ሰአት በፊትየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለትራምፕ ‘የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት’ አስተላለፉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ዶናልድ ትራምፕ እና ቤንያሚን ናታንያሁየሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ድል ማድረጋቸውን ማወጃቸውን ተከትሎ አንዳንድ የአለም መሪዎች የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።“እንኳን ደስ አለዎት በታሪካዊው ታላቅ ድል። ወደ ዋይት ሃውስ ያደረጉት ታሪካዊ መመለስ ለአሜሪካ አዲስ ጅምር እና በእስራኤል እና በአሜሪካ ላለው ታላቅ ጥምረት ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ተናግረዋል።አክለውም “ይህ ታላቅ ድል ነው” ብለዋል።የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚንስትር ቪክቶር ኦርባን በበኩላቸው “በአሜሪካ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ታላቅ መመለስ ነው። ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቅ ድልዎ እንኳን ደስ አለዎ። ለዓለም በጣም መሰረታዊ ድል ነው” ብለዋል።ትራምፕ በምርጫው ማሸነፋቸውን ቢያውጁም የሚያስፈልጋቸውን የኤሌክቶራል ኮሌጅ ድምጽ እስካሁን አላገኙም። ከሚያስፈልጋቸው 270 ድምጽ አራት የጎደላቸው ሲሆን ካማላ ሃሪስ ያገኙት 218 ነው።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመርም በበኩላቸው ዶናልድ ትራምፕን “በታሪካዊው ድል” እንኳን ደስ አለዎት ብለዋቸዋል።በሚቀጥሉት ዓመታት ከእርስዎ ጋር ለመስራት በጉጉት እጠብቃለሁ “ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር“እንደ ቅርብ አጋርነታችን፣ የጋራ በሆኑት የነጻነት፣ የዲሞክራሲ እሴቶቻችንን ለመጠበቅ አንድ ላይ ቆመናል” ሲሉ አክለዋል።ያጋሩ, የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለትራምፕ ‘የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት’ አስተላለፉ
- ከ 7 ሰአት በፊትትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ የምርጫ ውጤት ተቆጥሮ ባያልቅም የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” ብለዋል።ትራምፕ በመቀጠል ይህ የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን እንደሚሆን ተናግረዋል።“ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል” ሲሉም የምርጫ ዘመቻ መፈክራቸውን በመጠቀም ተናግረዋል።ትራምፕ የሚያስፈልጋቸውን 270 የኢሌክቶራል ኮሌጅ ድምጽ ማግኘታቸው ሳይታወቅ ድል ማድረጋቸውን ተናግረዋል።ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው በተናገሩበት የፍሎሪዳ መድረክ “አገራችን እንድትድን እንረዳታለን” ብለዋል።በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ፓርቲያቸው እና እሳቸው ታሪክ የሰሩት በምክንያት ነው ብለዋል።ትራምፕ በዚህ የድል ንግግራቸው ይህችን ዕለት “በህይወታችሁ ጠቃሚ የምትባል ዕለት አድርጋችሁ እንደምትቆጥሯት” ተስፋ አለኝ ብለዋል።“አሜሪካ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ስልጣን ሰጥታናለች” በማለት ፓርቲያቸው የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን የበላይነት ከዲሞክራቶች በመውሰድ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል።ያጋሩ, ትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” አሉ
- ከ 7 ሰአት በፊትሪፐብሊካኖች የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይቆጣጠራሉ- ትንበያ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየሪፐብሊካን ፓርቲ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ሴኔትን በበላይነት ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ የውጤት ቆጠራዎችን መሰረት ያደረጉ ትንበያዎች አሳዩ።አሁንም ቢሆን የምርጫው ውጤቶች ተቆጥረው ባያልቁም ዲሞክራቶች የህግ የመወሰኛ ምክር ቤት የበላይነታቸውን እንደሚያጡ ግልጽ ሆኗል።ለሁለት ዓመታት ያህል ሴኔቱን ዲሞክራቶች በበላይነት ተቆጣጥረው የነበረ ቢሆንም በኦሃዮ እና በዌስት ቨርጂኒያ የነበሩ የሴኔት መቀመጫቸውን ማጣታቸውን ተከትሎ ሪፐብሊካን አብላጫ ድምጽ ማግኘታቸው ተገልጿል።ዲሞክራቶች ለሁለት ዓመታት ያህል የህግ መወሰኛውን ምክር ቤት በጠባብ አብላጫ እየመሩ ነበር።ይህም 47 ዴሞክራቶች እና አራት ገለልተኛ ሴናተሮች ለፓርቲው ከ100 መቀመጫዎች ውስጥ 51 በማግኘት በበላይነት ተቆጣጥረው ነበር። ነገር ግን ማክሰኞ፣ ሁለት ሴናተሮች መሸነፋቸውን ተከትሎ ስልጣኑ ወደ ሪፐብሊካን እጅ ተመልሷል።ያጋሩ, ሪፐብሊካኖች የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይቆጣጠራሉ- ትንበያ
- ከ 7 ሰአት በፊትየምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersበአሜሪካ የመጨረሻዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች በአላስካ እና ሃዋይ ሲዘጉ እስካሁን ባሉ የቆጠራ ውጤቶች ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው።እስካሁን ባሉ የቆጠራ ውጤቶችን መሰረት ባደረጉ ትንበያዎች መሰረት ዶናልድ ትራምፕ 246 ኢሌክቶራል ኮሌጅ ድምጾችን እንዳገኙ ሲገመት የዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ ደግሞ 194 ኢሌክቶራል ኮሌጅ እንዳገኙ ይታመናል።አንድእጩ ዋይትሃውስን ለማሸነፍ 270 ኢሌክቶራልኮሌጅ ማግኘትአለበት።እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ምርጫ ወሳኝ ከሚባሉት ውስጥ የሰሜን ካሮላይና እና ጆርጂያ ግዛቶችን ትራምፕ ማሸነፍ ችለዋል። እስካሁን ድረስ የአምስት ተጨማሪ ወሳኝ ግዛቶች ውጤት ባይታወቅም ቀደምት ትንበያዎች ትራምፕ በሁሉም እየመሩ እንደሆነ አሳይተዋል።.እነዚህስፍራዎች ካማላሃሪስ ወይምትራምፕ ሊያሸንፉባቸው የሚችሉ ተለዋዋጭነት ያላቸው ሲሆን የምርጫ ውጤቱንም የሚወስኑ እንደሆነ ተነግሯል።የዲሞክራት ደጋፊዎች እና የምርጫው ስትራቴጂስቶች “ተስፋ የመቁረጥ ስሜት” እየተሰማቸው እንደሆነ ለቢቢሲው የምርጫ ዘጋቢ ተናግረዋል። በፍሎሪዳ የትራምፕ መቀመጫ ደግሞ ከፍተኛ ደስታ እየተገለጸ እንደሆነ ተዘግቧል።
የፎቶው ባለመብት,Reuters
የፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው
- ከ 8 ሰአት በፊትድሉ ወደ ትራምፕ እያጋደለ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ገና ቢሆንም እስካሁን ባሉ ቆጠራዎችን መሰረት ባደረጉ ትንበያዎች ድሉ ወደ ሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ እያጋደለ ነው።ትራምፕ ከወሳኝ ግዛቶች መካከል የተጠበቀውን የሰሜን ካሮላይና ግዛት ያሸነፉ ሲሆን ሌላኛዋን ወሳኟን ጆርጂያ ግዛትን ማሸነፍ እንደቻሉ ትንበያዎች አሳይተዋል።የኢሌክቶራል ውጤትን የሚያሳየው ካርታ ትራምፕ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው በተለየ በአውሮፓውያኑ 2016 ያሸነፉበትን መስሏል።በመላው አሜሪካ ውጤታቸውን ይፋ ባደረጉት ግዛቶች የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚታይ ልዩነት እየመሩ እንደሆነ አሳይቷል።ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በከተሞች እና በከፊል ከተሞች መካከል ያገኙት ድምጽ ከዚህ ቀደም ጆ ባይደን ካገኙት ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ልዩነት ማጥበብ አልቻሉም።
የፎቶው ባለመብት,Reuters
የፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, ድሉ ወደ ትራምፕ እያጋደለ ነው
- ከ 8 ሰአት በፊትትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛትን አሸነፉ
የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ወሳኝ ከሚባሉት መካከል የሰሜን ካሮላይናን ግዛት በማሸነፍ 16 ኢሌክቶራል ድምጽ ማግኘት ችለዋል።ፕሬዚዳንታዊ ውድድሩን ለማሸነፍ 270 ኢሌክቶራልኮሌጅ ድምጽማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ትራምፕ ይህ መልካም ዜና ነው።ነገር ግን አብዛኞቹ የወሳኝ ግዛቶች ውጤት ገና ያልታወቀ ሲሆን በተለይም የዊስኮንሰን፣ ፔንሲልቫንያ እና ሚቺጋንን የያዙት ‘ረስት ቤልት ሲት’ ግዛትን የሚያሸንፉ ከሆነ ድሉ ወደ ካማላ ሃሪስ ሊያጋድል ይችላል̄።የሰሜን ካሮላይና ድል ለሪፐብሊካኖች ትልቅ ቢሆንም ግዛቲቱ ከዚህ በፊት ድምጽ ከምትሰጥበት ጋር ተመሳሳይ ነው። በአውሮፓውያኑ 2016 በነበረው ምርጫ በ3.66 በመቶ ልዩነት ያሸነፉ ሲሆን በ2020 ደግሞ ባነሰ 1.34 ማሸነፋቸው ይታወሳል።ያጋሩ, ትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛትን አሸነፉ
- 5 ህዳር 2024በጆርጂያ በሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች የተነሳ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ምርጫ ተቋረጠ
የፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/REX/SHUTTERSTOCKየምስሉ መግለጫ,በአትላንታ መራጮች የምርጫ ወረቀታቸውን ስካን ለማድረግ ሲዘጋጁበጆርጂያ አምስት ሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች ነበሩ ሲል የቢቢሲ የአሜሪካ ሚዲያ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ዘግቧል።የአካባቢው የምርጫ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ናዳይን ዊሊያምስ በዛቻው የተነሳ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በግምት ለ30 ደቂቃዎች ቦታውን ለቀው ወጥተው ነበር ብሏል።አካባቢው አትላንታ ከተማን የሚያካትት ሲሆን፣ በሁለቱ ስጋቱ ተከስቶባቸው በነበሩ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ሰዓትን ለማራዘም የፍርድ ቤት ይሁንታን ለማግኘት እየተሞከረ እንደሆነ አስታውቋል።በተመሳሳይ ዜና በፔንሴልቫንያ እንዲሁ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መራጮች የምርጫ ወረቀታቸውን ስካን ማድረግ ባለመቻላቸው የተነሳ ለባከኑ ሰዓታት የምርጫ ሰዓቱን ለማራዘም ለፍርድ ቤት ጥያቄ መቅረቡ ተሰምቷል።ያጋሩ, በጆርጂያ በሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች የተነሳ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ምርጫ ተቋረጠ
- 5 ህዳር 2024የአሜሪካን ምርጫ የሚወስነው ምንድን ነው?
የፎቶው ባለመብት,AFPበአሜሪካ የፖለቲካ ታሪክ እንደዘንድሮው ምርጫ ፉክክሩ ጦዞ አያውቅም።ከዚህ ቀደም የተደረጉ ምርጫዎችን መለስ ብሎ ለሚያይ እኤአ በ2000 ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በአል ጎር ላይ የተቀዳጁት ድል በፍሎሪዳ ባገኙት በትንሽ መቶዎች የሚቆጠር የአብላጫ ድምጽ እንደነበር ይረዳል።በአሜሪካ ሁሌም ምርጫው ለማን ያዘነበለ እንደሆነ የሚታወቅበት ዕድል አለ።በአውሮፓውያኑ 2016 የተካሄደው ምርጫ ላይ ግን ይህ ግምት የተዛባ ሆኖ ተገኝቷል።በዚያ ዓመት የመራጮችን አስተያየት የሚገምቱ ሁሉ ዕድል ፊቷን ወደ ሒላሪ ክሊንተን ታዞራለች ሲሉ ተንብየው ነበር።በኋላ እንደታየው ግን ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊ ሆነው ወጥተዋል።በአሁኑ ምርጫ ግን የምርጫው ውጤት ለሁለቱም ያደላ መሆኑን የሚያሳዩ ትንበያዎች በርካታ ናቸው።ማንም ደፍሮ አንዱ ያሸንፋል ሊል አልቻለም። ሙሉውን ዘገባ እዚህ ያንብቡ የአሜሪካን ምርጫ የሚወስነው ምንድን ነው?ያጋሩ, የአሜሪካን ምርጫ የሚወስነው ምንድን ነው?
- 5 ህዳር 2024አሜሪካውያን ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በተጨማሪ ለሌሎች ጉዳዮችም ድምጽ እንሚሰጡ ያውቃሉ?
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,መራጮች ለተለያዩ ጉዳዮች ድምጽ እንዲሰጡ የሚቀሰቅሱ ፖስተሮችባለፉት ወራት ስለ አሜሪካ ምርጫ ሲወራ ዋነኛው እና ብቸኛው ጉዳይ በካማላ ሃሪስ እና በዶናልድ ትራምፕ መካከል ስለሚደረገው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ነው። በእርግጥም ፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ለአሜሪካውያን መራጮች ዋነኛው ጉዳይ ነው። ነገር ግን መራጮች ለተጨማሪ ጉዳዮች ድምጽ ይሰጣሉ።በዛሬው ዕለት በሚጠናቀቀው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት አሜሪካውያን መራጮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣሉ። በዚህም መሠረት ግዛቶች በሚከተሉት ሕጎች እና የምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ድምጽ ይሰጣሉ።
- ጽንስን የማቋረጥ መብትን በተመለከተ ከባድ ፉክክር የሚደረግባቸውን አሪዞና እና ኔቫዳን ጨምሮ በአስር ግዛቶች ውስጥ ድምጽ ይሰጣል።
- ለአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አንድ ሦስተኛ መቀመጫዎች ማለትም ካሉት 100 መቀመጫዎች ለ34ቱ አባላትን ይመርጣሉ። በአሁኑ ወቅት ዲሞክራቶች በአንድ ድምጽ የበላይነት ሴኔቱን ይቆጣጠሩታል።
- በየሁለት ዓመቱ ለሚመረጡት 435 የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ኮንግረስ) አባላት ምርጫ ይደረጋል። በአሁኑ ወቅት ሪፐብሊካን ጠባብ የበላይነት አላቸው።
- ለመዝናኛነት እና ለህክምና አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውል የማሪዋና ዕጽ አጠቃቀምን በተመለከተ የፍሎሪዳ፣ ኔብራስካ፣ ሰሜን ካሮላይና እና ደቡብ ካሮላይና ነዋሪዎች ድምጽ ይሰጣሉ።
- ምርጫን እና ድምጽ አሰጣጥን በተመለከተ ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል፤ በዚህም በአንዳንድ ግዛቶች መራጮች ምርጫዎች እንዴት መካሄድ እንዳለባቸው ውሳኔ ይሰጣሉ።
- 5 ህዳር 2024በአሜሪካ የድምጽ መስጫ ጣብያዎች ተከፍተዋልበአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች መራጮች ድምጻቸውን መስጠት ጀምረዋል።ሰሜን ካሮላይና፣ ኢንዲያና፣ ኬንታኪ፣ ኒው ጀርሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ፍላዴልፊያ፣ ፔንሴልቫኒያ፣ ቨርጂኒያ፣ ጆርጂያ መራጮች ድምጻቸውን መስጠት ከጀመሩባቸው ግዛቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።
የምስሉ መግለጫ,መራጮች በፔንሴልቫኒያ ድምጻቸውን ለመስጠት ሰልፍ ይዘው ይታያሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በአትላንታ ጆርጂያ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ሲገቡ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በኒውዮርክ የመጀመሪያዎቹ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ተሰልፈው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በኒውዮርክ የመጀመሪያዎቹ መራጮች ድምጻቸውን ሰጥተዋልያጋሩ, በአሜሪካ የድምጽ መስጫ ጣብያዎች ተከፍተዋል
- 5 ህዳር 2024ሩሲያ በምርጫው እምነት እንዲጠፋ ጥረት እያደረገች ነው – የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበርካታ ታዋቂ አሜሪካዊያን ድምፃቸውን ለማን እንደሚሰጡ ይፋ እያደረጉ ነው። ታዋቂዋ ሙዚቀኛ ሌዲ ጋጋ ድምጿን ለካማላ ሃሪስ እንደምትሰጥ ይፋ ስታደርግ ጆ ሮጋን የተባለው ታዋቂ የፖድካስት ጋዜጠኛ ደግሞ ድጋፉን ለትራምፕ እንደሚሰጥ አስታውቋል።ከዚህ ዜና ወጣ ስንል የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች “የውጭ ኃይሎች” የአሜሪካ ምርጫ እምነት እንዲያጣ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ወቅሰዋል።መሥሪያ ቤቶቹ ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ኃይሎች “ሕዝቡ በአሜሪካ ምርጫ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር እና ክፍፍል እንዲሰፍን” ሙከራ እያደረጉ ነው ብለዋል።የብሔራዊ ደኅንነት ዳይሬክተር ቢሮ፣ ኤፍቢአይ እና የሳይበርሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች የምርጫ አስተባባሪዎች ላይ አመፅ እንዲነሳ እያደረጉ ነው እንዲሁም ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል ሐሰተኛ ዜና እያሰራጩ ነው ብለዋል።“በሩሲያ ተፅዕኖ ሥር ያሉ ቡድኖች” በቅርቡ የምርጫ አስተባባሪዎች በተለይ በቁልፍ ግዛቶች የምርጫ ሳጥኑን በመሙላት ምርጫውን ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል የሚል ሐሰተኛ ዜና መለጠፋቸውን መግለጫው ጠቅሷል።መግለጫው አክሎ በሚቀጥሉት ቀናት መሰል ዜናዎች የበለጠ ሊሰራጩ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳለ አስታውቋል።መሥሪያ ቤቶቹ በጋራ ያወጡት መግለጫ ኢራን ለአሜሪካ “ከፍተኛ የውጭ ስጋት ናት” ይላል።ቴህራንም ሆነች ሞስኮው በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ ነው የሚለውን ዜና ያስተባብላሉ።ያጋሩ, ሩሲያ በምርጫው እምነት እንዲጠፋ ጥረት እያደረገች ነው – የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች
- 5 ህዳር 2024ምርጫውን ካማላ ሃሪስ ወይም ዶናልድ ትራምፕ ሊያሸንፉ የሚችሉባቸው 10 ነጥቦች
ሁለቱም ዕጩዎች ወሳኝ በሚባሉ ቦታዎች ደጋፊዎቻቸው በነቂስ ወጥተው እንዲደግፏቸው የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳዎች ሲያካሂዱ ቆይተዋል።ከሁለቱ ዕጩዎች አንዱ ይህን ታሪካዊ የተባለ ምርጫ ሊያሸንፉባቸው የሚችሉ 10 ነጥቦችን እነሆ።ዝርዝር ዘገባ – ምርጫውን ካማላ ሃሪስ ወይም ዶናልድ ትራምፕ ሊያሸንፉ የሚችሉባቸው 10 ነጥቦች