November 6, 2024 – VOA Amharic
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ፉክክር የተደረገባቸውን እንደ ፔንሴልቫኒያ እና ዊንስኮንሰን ያሉ ወሳኝ ግዛቶች ማሸነፋቸውን ተከትሎ፣ ረቡዕ ጠዋት የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ማሸነፋቸውን ተረጋግጧል።
ይህ ውጤት ይፋ ከመደረጉ ቀደም ብሎ ኢትዮጵያውያን ከመጪው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ምን እንደሚጠብቁ ጠይቀናቸው ነበር።