November 19, 2024 

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፣ ኮሚሽኑ የቀረው የሥራ ዘመን ሦስት ወር ቢኾንም የቆይታ ጊዜው እንዲራዘም መጠየቅ እንደማይፈልጉ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አስታውቀዋል።

ከታጠቁ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ምክክር ስለመኖሩ ለተነሳው ጥያቄ፣ ወደ ኮሚሽኑ ለውይይት የመጣ የታጠቀ ኃይል እንደሌለ ፕሮፌሰር መስፍንተናግረዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ከ1 ሺሕ 400 ወረዳዎች ውስጥ በ615ቱ አጀንዳ ማሰባሰቡን የጠቀሱት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ከኮሚሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት በተፈራረሙ ማግስት አባሎቻቸው የሚታሠሩባቸው ፓርቲዎች አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ቁርጥ ያለ ጊዜ ባያስቀምጡም፣ በትግራይ በቅርቡ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደሚጀም ጠቁመዋል።