November 20, 2024 – Konjit Sitotaw 

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ፣ ከጸደቀ ዓመት ያልሞላው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር የሠራተኞች ደንብ እንደተሻረ አስታውቋል፡፡

ከእንግዲህ ፍርድ ቤቶች በአዲሱ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት እንደሚተዳደሩ ተገልጧል።

ደንቡ የጸደቀው፣ ፍርድ ቤቶች ከልዩ ባሕሪያቸው አንጻር በአደረጃጀትና አስተዳደር ሙሉ ተቋማዊ ነጻነትና ገለልተኝነት ኖሯቸው እንዲሠሩ ለማስቻል ነበር።

ፍርድ ቤቶች እንደ አስፈጻሚ ተቋም በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ መካተታቸው የገለልተኝነት ችግር አይፈጥርም ወይ? የሚል ጥያቄ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት አንስተው ነበር። ኾኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመሩት የሜሪትና የደመወዝ ቦርድ ስለሚቋቋም፣ ፍርድ ቤቶች ቦርዱ በሚሰጣቸው ውክልና መሠረት ገለልተኛ ኾነው መስራት ይችላሉ የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።