November 23, 2024 

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ባንድ ወጣት ላይ የተፈጸመውን ግድያ መንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ፋኖ በአካባቢው ሕዝብ ላይ በጋራ ጥቃት ይፈጽማሉ ለሚል ቅስቀሳ ወደፊት ሊጠቀምበት አቅዶ ነበር ሲል ወቅሷል።

ኾኖም የግድያው ተንቀሳቃሽ ምስል በድንገት ይፋ መኾኑን ተከትሎ፣ መንግሥት በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች መካከል ቁርሾ ለመፍጠር ተጠቅሞበታል በማለት ቡድኑ ከሷል።

ቡድኑ፣ በወጣቱ ላይ ግድያውን የፈጸሙት፣ ባካባቢው በመንግሥት ወኪሎች የሚደገፉ ራሳቸውን ፋኖ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች መኾናቸን ደርሼበታለኹ ብሏል።

የመንግሥት አካሄድ በአገሪቱ ሕልውና ላይ ከባድ አደጋ ደቅኗል ያለው ቡድኑ፣ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግ ጠይቋል።