November 25, 2024 – Konjit Sitotaw

ፒያሳ ‘ቻይና ግቢ’ የእሳት አደጋ ተከሰተ
ፒያሳ ከሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት ፊት ለፊት በተለምዶ ‘ቻይና ግቢ’ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ዛሬ ከሰአት 9 ሰአት ገደማ ነው የእሳት አደጋው መከሰቱ የተነገረው፡፡
“ዘጠኝ ሰአት የተነሳው እሳት አሁንም አልጠፋም፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው ተገኝተዋል” ያለው አንድ በስፍራው የሚገኝ ግለሰብ እሳቱ እየቆየ የቀነሰ ይመስል እና እንደገና ይጨምራል በማለት ተናግሯል።
የእሳት አደጋው ‘ጃንጉሲ ኮንስትራክሽን’ በተባለ ድርጅት ውስጥ እንደተነሳ ታውቋል።
ከሰሞኑ በተመሳሳይ በመርካቶ በቀናት ልዩነት ሁለት ግዜ ከባድ የእሳት አደጋዎች መከሰታቸው ይታወሳል።

