
ከ 5 ሰአት በፊት
ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ያጯቸው በርካታ የካቢኔ አባላት እና የዋይት ሐውስ ተሿሚዎች የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ ደረሳቸው።
ኤፍቢአይ የተባለው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ “በርካታ የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪዎች” መድረሳቸውን ገልጿል።
ቢሮው እንዳለው በርካታ ሐሰተኛ የስልክ ጥሪዎች የተደረጉት ፖሊስ ዒላማ ይሆናሉ ወደተባሉ ሰዎች መኖሪያ ቤት እንዲመጣ ነው።
ዕጩ የመከላከያ፣ የቤቶች፣ የግብርና ሚኒስትሮች ዛቻ ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ሲሆኑ በተባበሩት መንግሥት የአሜሪካ ተወካይ ይሆናሉ የተባሉትም ግለሰብ እንዲሁ ዒላማ ሆነዋል።
አዳዲሶቹ የትራምፕ የካቢኔ አባላት ማስፈራሪያ የደረሳቸው ማክሰኞ ምሽት እና ረቡዕ መሆኑን ያሳወቀው ፖሊስ ምርመራ መክፈቱን ገልጿል።
የትራምፕ የሽግግር መንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት ካሮላይን ሌያቪት የትራምፕ ተሿሚዎች “በጣም አስፈሪና እና አሜሪካዊ ባልሆነ ሁኔታ ነው ከነቤተሰቦቻቸው ነው ዛቻ የደረሰባቸው” ብለዋል።
የተመራጮቹን ደኅንነት ለመጠበቅ “ሕግ አስከባሪዎች በፍጥነት ሁኔታውን ተቆጣጥረውታል” ሲሉም አክለዋል።
ቃለ አቀባይዋ ጨምረው “ምንም ዓይነት ማስፈራሪያ እና አመፅ እንደማይገታን ፕሬዝደንት ትራምፕ ጥሩ ማሳያ ናቸው” ብለዋል።
ኤፍቢአይም ሆነ የትራምፕ የሽግግር መንግሥት ቡድን ማስፈራሪያ የደረሰባቸውን ሰዎች ስም ይፋ አላደረጉም።
- “ወደ ቤታችን ልንመለስ ነው፤ ደስ ብሎናል” – በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንከ 6 ሰአት በፊት
- በሊባኖስ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ስለምን በጋዛ አልሳካ አለ?ከ 6 ሰአት በፊት
- አዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ለአፍሪካ ምን ይዘው ይመጣሉ?27 ህዳር 2024
ትራምፕ በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ የመረጧቸው ኤሊስ ስቴፋኒክ ዛቻ እንደደረሰባቸው ያሳወቁ የመጀመሪያዋ ግለሰብ ሲሆኑ እሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ዕጩው የመከላከያ ሚኒስትር ፒተር ሄግሴዝ በተመሳሳይ የግድያ ዛቻ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል።
በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ማኅበራዊ ሚድያ ገፃቸው ይህን ያሳወቁት ሄግሴዝ ረቡዕ ጠዋት ዛቻ እንደደረሰባቸው ገልፀው “ማንኛውም ማስፈራሪያ ትራምፕ የጣሉብኝ አደራ ከማስፈፀም አያግደኝም” ብለዋል።
በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራ የተቃጣባቸው ፕሬዝደንት ትራምፕ የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ ከደረሳቸው ሰዎች መካከል አለመሆናቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን አስታውቀዋል።
መገናኝ ብዙኃን እንደሚሉት የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ የደረሰባቸው ዕጩ ተሿሚዎች ሴክሬት ሰርቪስ በተባለው የደኅንነት መሥሪያ ቤት ጥበቃ እየተደረገላቸው አይደለም።
የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሆኑ በትራምፕ የተመረጡት ሊ ዜልዲን ደግሞ “ለፍልስጤም ድጋፍ ያለው የሚመለስል” መልዕክት ያለበት የቦምብ ጥቃት ዛቻ ደርሶብኛል ብለዋል።
አዲሱን የትራምፕ አስተዳደር ለማገልገል ከተሾሙ ሰዎች መካከል በርካታዎቹ ዛቻ እንደደረሰባቸው ኤፍቢአይ አስታውቆ ከሌሎች የፀጥታ መሥሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት ጥበቃውን ማጠናከሩን ገልጿል።
ትራምፕ ላይ የቀረበውን የወንጀል ክስ የሚመለከቱ ሰዎች ላይ በቅርቡ ተመሳሳይ የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ይታወሳል።
ባለፈው ዓመት በገና በዓል ወቅት የአሜሪካ ፖለቲከኞች በተመሳሳይ የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ ደርሶባቸውን እንደነበር አይዘነጋም።
ዕጩ