
ከ 4 ሰአት በፊት
ማህሙድ ከዕድሜ እኩዮቹ ጋር ሲጫወት የፊት ጥርሱን ቢያጣም የሚያምር ፈገግታውን አልሸፈነበትም።
ሱዳናዊው ማህሙድ ወላጆቹን ማጣቱ ሳያንስ በአገሩ አስከፊ ጦርነት ሁለት ጊዜ ለመፈናቀል ተገዷል። ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሯል በተባለለት ጦርነት ምክንያት ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሱዳናውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
ዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃይ ያሉባት አገር ሆናለች። ብዙዎችም በረሃብ ለመኖር ተገደዋል።
በአንድ አካባቢ ረሃብ መከሰቱ ታውጇል። ሌሎች ደግሞ በቀጣይ ምግብ ከየት እንደሚያገኙ ባለማወቅ በረሃብ አፋፍ ላይ ይኖራሉ።
አዲሱ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድርጅት ኃላፊ ቶም ፍሌቸር “የማይታይ ቀውስ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
“ከግማሽ በላይ የሚሆኑት (ሃያ አምስት ሚሊዮን) ሱዳናውያን እርዳታ ይፈልጋሉ” ሲሉም አክለዋል።
እንደጋዛ እና ዩክሬን ባሉ ቦታዎች አስከፊ ጦርነቶች መከሰታቸው የእርዳታ እና የትኩረት መበታተን ፈጥሯል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ነው የሱዳንን ችግር ለማጉላት በማለት ፍሌቸር ለመጀመሪያ ተልዕኳቸው ሱዳንን የመረጡት።
“ይህ ቀውስ ለተባበሩት መንግስታት፣ የሱዳንን ህዝብ ለመርዳት ህይወታቸውን ለሚያጡ በግንባሩ ላሉት ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪዎች የሚታይ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በእርሳቸው ቡድን ውስጥ የሚሠሩት አብዛኛዎቹ ሱዳናውያን በአገሪቱ ጦር እና በአርኤስኤፍ መካከል ባለው የሥልጣን ሽኩቻ ቤታቸውን፣ የቀድሞ ሕይወታቸውን ያጡ ናቸው።
የፍሌቸር የመጀመሪያ ጉብኝት በምስራቅ ሱዳን ከሰላ ወደ ሚገኘው እና ማህሙድ ወደሚገኝበት ሜይጎማ የህጻናት ማሳደጊያ ወስዷቸዋል። ጉዳት የደረሰበት ባለ ሦስት ፎቅ ትምህርት ቤትን ወደ መጠለያነት በመቀየር ወደ 100 የሚጠጉ ህጻናት ተጠልለውበታል።

- “ወደ ቤታችን ልንመለስ ነው፤ ደስ ብሎናል” – በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንከ 6 ሰአት በፊት
- በርካታ የትራምፕ ዕጩ የካቢኔ አባላት የቦምብ ጥቃት ማስፈራሪያ ደረሰባቸውከ 5 ሰአት በፊት
- በሊባኖስ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ስለምን በጋዛ አልሳካ አለ?ከ 6 ሰአት በፊት
እአአ ሚያዝያ 2023 የአገሪቱ ጦር እና አርኤስኤፍ አባላት ጦር ተማዘው አገራቸውን ወደ አሰቃቂ ብጥብጥ፣ ስልታዊ ዘረፋ እና አስደንጋጭ እንግልት ውስጥ እስኪከቱ ድረስ ህጻናቱ በዋና ከተማዋ ካርቱም ይኖሩ ነበር።
ጦርነቱ በመካከለኛው ሱዳን ዋድ ማዳኒ ወደሚገኘው አዲሱ መጠለያ ባለበት አካባቢ በተስፋፋበት ወደ ከሰላ ሸሹ።
የ13 ዓመቱ ማህሙድ ምኞቱ ምን እንደሆነ ሲጠየቅ ወለቀ ጥርሱን ሳይደብቅ ፈገግ
“አስተዳዳሪ ሆኜ የፈረሱ ቤቶችን መገንባት እፈልጋለሁ” ሲል መለሰ።
ከአንድ መጠለያ ወደ ሌላኘው ለተፈናቀሉት 11 ሚሊዮን ሱዳናውያን ወደ ተረፈችው ቤታቸው መመለስ እና ህይወታቸውን መገንባት የሁሉም ትልቁ ምኞት ነው።
አሁን ግን ምግብ ማግኘት እንኳን የዕለት ተዕለት ትግል ሆኗል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ለማድረግ ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል።

ፍሌቸር በፖርት ሱዳን ካደረጉት የአራት ቀናት ስብሰባዎች በኋላ፣ የተባበሩት መንግስታት ተጨማሪ የአቅርቦት ማዕከላትን ለማቋቋም እና ተጨማሪ ሦስት አየር ማረፊያዎችን እንዲጠቀም ፍቃድ መስጠታቸውን የጦር ኃይሉ አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን በኤክ ገጻቸው አስፍረዋል።
አንዳንዶቹ ፈቃዶች ከዚህ በፊት ተሰጥተው ነበር ቢሆንም የአሁንን ውሳኔ አንድ እርምጃ የሄደ ነው ሲሉ አንዳንዶች ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ደብሊውኤፍፒ) በአርኤስኤፍ ቁጥጥር ስር ያሉ እና የተጎዱ ማህበረሰቦችን ለመድረስ ፈቃድ አግኝቷል። በቅርቡ ረሃብ የተረጋገጠበት እና ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን የሚያስተናግደው የዳርፉሩ ዘምዘም መጠለያ ጣብያ አንዱ ነው።
“ወደ እነዚህ ማህበረሰቦች ለመድረስ ለወራት ስንጥር ነበር” ሲሉ በፖርት ሱዳን የደብሊውኤፍፒ ኃላፊ የሆኑት አሌክስ ማሪያኔሊ ተናግረዋል።
በደብሊውኤፍፒ መጋዘን ውስጥ የሚሠሩ ሱዳናውያን የከፋ አደጋ ለተጋረጠባቸው አካባቢዎች የሚከፋፈሉ የምግብ ካርቶኖችን የጭነት መኪናዎች ላይ ይጭናሉ።
እንደዚህ ባለ አስቸጋሪ እና አደገኛ አካባቢ ሠርተው እንደማያውቁ ማሪያኔሊ ተናግረዋል።
ጄኔራል ቡርሃን የሱዳን ገዥ ናቸው በሚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዕውቅና መስጠቱ እጁ እንዲታሰር አድርጎታል በማለት አንዳንዶች ሰብዓዊ ተቋማት ድርጅቱን ይወቅሳሉ።
“ጄነራል ቡርሃን እና ባለሥልጣናቱ እነዚያን የኬላዎችን፣ የፈቃድ መስጫ እና ስርዓቱን ይቆጣጠራሉ” ሲሉ ፍሌቸር ምላሽ ሰጥተዋል።
“ወደ እነዚያ አካባቢዎች መሄድ ከፈለግን እነሱን ፈቃድ ማግኘት አለብን።”
ተቀናቃኙ አርኤስኤፍም ሕዝቡን እንደሚያስቀድም ተስፋ ያደርጋሉ።
ፍሌቸር አክለውም “እርዳተውን ለማግኘት እና ህይወት ለማዳን የትም እሄዳለሁ፤ ማንም አነጋግራለሁ” ብለዋል።
በአስከፊው የሱዳን ጦርነት ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል በሚል ተከሰዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሱዳን ውስጥ እንደ “ወረርሽኝ” የሚቆጥረው ወሲባዊ ጥቃትም ጥቅም ላይ ውሏል።
የተባበሩት መንግስታት ጉብኝት ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለማስቆም በአለም አቀፍ ደረጃ በሚከበረው “የ16 ቀናት እንቅስቃሴ” ዘመቻ ጋር ገጥሟል።
በፖርት ሱዳን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያ ውስጥ የተደረገው ዘመቻ በተለየ መልኩ ልብ የሚነካ ነበር።
“ከዘህ በተሻለ መሥራት አለብን፣ የተሻለ መስራት አለብን” ሲሉ ፍሌቸር ከሱዳናውያን ሴቶች እና ህጻናት የቀረበላቸውን ጭብጨባ እና እልልታ ተከትሎ የያዙትን መድረክ ንግግር ጽሑፍ ትተው ተናግረዋል።

ንግሩን ያዳመጡ አንዳንድ ሴቶችን ቢቢሲ አናግሯል።
“እርዳታ ቢያስፈልግንም ግን ዋናው ሥራ ከራሳቸው ከሱዳናውያን መሆን አለበት” በማለት ለአገር ውስጥ የእርዳታ ድርጅት የምትሠራው ሮሚሳ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ በካርቱም የገጠማትን አስከፊ ጉዞ ትናገራለች።
“የሱዳን ህዝብ በአንድነት የሚቆምበት ጊዜ አሁን ነው።”
ሱዳኖች በጥቂቱምቢሆን ብዙ ነገር ለማድረግ ሲጥሩ ቆይተዋል።
ባለ ሁለት ክፍል መጠለያ ውስጥ ሻማ የሚባል ደህንነቱ የተጠበቀ ቤት በደል ለደረሰባቸው ሴቶች እና ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የተወሰነ ብርሃን እየሰጠ ነው።
መስራቿ ኑር ሁሴን አል ሰዋቲ ወይም እማማ ኑር በመባል የሚታወቁት ግለሰብም በሜይጎማ የህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ መኖር ጀምረዋል።
በስራቸው ያሉትን ለመጠበቅ ከካርቱም መውጣት ተገደዋል። እሳቸው ዘንድ ከተጠለሉት አንዷ ከጦርነቱ በፊት ተደፍራለች፤ ከዚያ በሏላም ታፍና እንደገና ተደፍራለች።
ጠንካራ የነበሩት እማማ ኑር ጭምር አሁን ላይ ተዳክመዋል።
“በጣም ደክሞናል፡ እርዳታ እንፈልጋለን” ብለዋል።
“ንጹህ አየር መማግ እንፈልጋለን። አሁንም በዓለም ላይ ስለእኛ ስለሱዳናዊያ የሚያስቡ ሰዎች እንዳሉ እንዲሰማን እንፈልጋለን።”