November 28, 2024 – VOA Amharic
አሜሪካውያን በየዓመቱ አንድ መቶ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በየዓመቱ በሚዘጋጀው የሜሲስ ምስጋና ቀን የሰልፍ ትዕይንት ሲደሰቱ ኖረዋል። በነዚህ ዓመታት ውስጥ የተቋረጠው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ብቻ ነበር። “ሜሲስ” በተባለው ታዋቂ ግዙፍ መደብር የሚዘጋጀው ትዕይንት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሸማቾችን “የኛ” በሚል ስሜት ከመደብሩ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ዓመታዊ በዓል ነው።