November 28, 2024 – VOA Amharic
የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ የችሎቱ ዳኞች የሚያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መሪ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጡ ጠይቀዋል። ትዕዛዙ እንዲወጣ የተጠየቀው በሚያንማር በሚገኙ የሮሄንጂያ ሙስሊም ሕዳጣን ማኅበረሰብ ላይ መፈናቀል እና ሰቆቃን ጨምሮ የሰብአዊ ወንጀል ተፈጽሟል በሚል ነው።
እ.አ.አ በ2021 በኦን ሳን ሱ ቺ ላይ መፈንቅለ መንግሥት አካሂደው ሥልጣን የተቆናጠጡት ጀኔራል …