November 28, 2024 – VOA Amharic
በአፍሪካ የተፈናቃዮች ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን እና 35 ሚሊዮን መድረሱን ዓለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ተናቃዮች ተከታታይ ማዕከል ይፋ ያደረገው ዐዲስ ሪፖርት አመለከተ። ከእነዚህም ውስጥ ቁጥራቸው 32.5 ሚሊዮን የሚደርሱት በግጭት እና ሁከት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ናቸው።
ትላንት ማክሰኞ የታተመው ሪፖርት አያይዞም፤ በአህጉሪቱ ያለውን በሃገር ውስጥ የመፈናቀል ፈተ…