የኤችአይቪ ኤድስ ምልክት

ከ 8 ሰአት በፊት

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ የሚያዙ እንዲሁም እያስከተለ ያለው ሞት በከፍተኛ ደረጃ ቢቀንስም የሕዝብ ስጋትነቱን ለማስቆም ዓለም በመንገድ ላይ እንዳልሆነች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራም (ዩኤንኤድስ) አጠነቀቀ።

ኢትዮጵያ በኤችአይቪ/ኤድስ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር በመቀነስ ረገድ ባለፉት አስራ አራት ዓመታት ጥሩ እመርታ ካሳዩ የአፍሪካ አገራት መካከል የተጠቀሰች ሲሆን፣ ይህም 60 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

እንደ ዩኤንኤድስ ከሆነ በዓለማችን ላይ 39.9 ሚሊዮን ሰዎች ኤድስ በደማቸው ያለባቸው ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ግማሾቹ በደቡብ እና ምሥራቃዊ አፍሪካ ይገኛሉ።

በዓለማችን ላይ በኤችአይቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ በ39 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፣ በኤድስ የሚሞቱትም እንዲሁ በግማሽ ቀንሷል።

ነገር ግን በአፍጋኒስታን፣ ግብፅ፣ በፊጂ፣ በፊሊፒንስ፣ በፓፕዋ ኒው ጊኒ እና በሳዑዲ አረቢያ በአውሮፓውያኑ 2010 – 2023 ባለው ጊዜ በኤችአይቪ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ፐርሰንት በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

ኬንያ፣ ማላዊ፣ ዚምባብዌ እና ኔፓል ኤችአይቪ/ኤድስን ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ በተሳካ ሁኔታ በ75 በመቶ መቀነስ የቻሉ አገራት ናቸው።

እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ኤድስን በመዋጋት ረገድ አፍሪካ እንደ አህጉር ቀዳሚውን ቦታ ይዛለች።

ሌሎች 18 አገራት ደግሞ ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ በየዓመቱ በኤችአይቪ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር 60 በመቶ መቀነስ ችለዋል።

አብዛኞቹ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት ሲሆኑ እነሱም ሌሶቶ፣ ኢስዋቲኒ፣ ቤኒን፣ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ቦትስዋና፣ ኤርትራ፣ ላይቤሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቶጎ፣ ዛምቢያ፣ ቡሩንዲ፣ ጊኒ ቢሳው እንዲሁም ታጂኪስታን፣ ፖርቹጋል፣ ቤላሩስ እና ጣልያን ናቸው።

ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ካሉ የዓለማችን ሕዝቦች መካከል 77 በመቶ የፀረ- ኤችአይቪ መድኃኒቶችን ይወስዳሉ። ከሰሃራ በታች ወዳሉ አገራት ስንመጣ ደግሞ 82 በመቶ የፀረ ኤችአይቪ መድኃኒቶች እንደሚወስዱ መረጃዎች ያሳያሉ።

የኤችአይቪ ቀውስን ለመግታት በተደረገው ትግል ምክንያት የሰው ልጅ አማካይ ዕድሜን ማሳደግ ተችሏል። በአውሮፓውያኑ 2010 የሰው ልጅ አማካይ እድሜ 56 የነበረ ሲሆን፣ በአውሮፓውያኑ 2013 ወደ 61 አድጓል።

በአፍሪካ ያለው የህክምና መስፋፋት በኤችአይቪ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በደማቸው ያለው የቫይረስ ጫና መጠን እንዳይጨምር እንዲሁም የመተላለፍ አደጋን እንዲቀንስ ማስቻሉን ዩኤንኤድስ ገልጿል።

ሆኖም የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል ያደረጉ እና መድኃኒትን መጠቀም የከለከሉ በርካታ አገራት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ህክምና እንዳያገኙ እንቅፋት ሆነዋል ተብሏል።https://flo.uri.sh/visualisation/20507559/embed?auto=1

መድኃኒት እየዋጠች ያለች ግለሰብ

ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የታየው መሻሻል

“በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የተሰጠው ምላሽ እንደ የማኅበረሰብ ንቅናቄ፣ ሕዝብ መር እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሊያስገኝ የሚችለውን ስኬት ያሳየ ነው” ሲሉ የዩኤንኤድስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ክሪስቲን ስቴግሊንግ ተናግረዋል።

የአገራት መሪዎች በተቻለ መጠን የመከላከል አማራጮችን በማስፋት እና ሰዎች የጤና አገልግሎቶችን እንዳያገኙ የሚያደርጉ እንቅፋቶችን የማስወገድ ተግባራት ላይ ማተኮር አለባቸው ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት የኢሜይል ምላሽ ገልጸዋል።

“ዓለም ኤድስን እንደ የሕዝብ ጤና ስጋት የማስወገድ ጎዳና ላይ አይደለም ምክንያቱም በአገልግሎት ተደራሽነት ላይ በተለይም የተገለሉ ማኅበረሰቦችን በማካተት ደረጃ ሰፊ ክፍተቶች ይታያሉ። ኤችአይቪን በመከላከል ረገድ ያለው ቀውስ አሁንም ቀጥሏል” ብለዋል።

ምንም እንኳን ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት ከፍተኛ እመርታ ቢታይም በአንዳንድ አገራት ደግሞ ከፍተኛ ማሻቀብ አሳይቷል።

በአፍጋኒስታን፣ በግብፅ፣ በፊጂ፣ በፊሊፒንስ፣ በፓፕዋ ኒው ጊኒ እና በሳዑዲ አረቢያ በአውሮፓውያኑ 2010 – 2023 ባለው ጊዜ በኤችአይቪ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ100 ፐርሰንት በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

ከአጠቃላይ ሕዝባቸው ጋር ሲነጻጸር እንደ አፍጋኒስታን፣ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ባሉ አገራት በኤችአይ የተያዙ ሰዎች በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ነው።

ሆኖም መጪው ጊዜ ብሩህ ይመስላል። የፖለቲካ እና የገንዘብ ድጋፍ ጋር ኤችአይቪ/ኤድስ በዓለም አቀፍ የኅብረተሰብ የጤና ስጋት መሆን በስድስት ዓመታት ውስጥ ማስቆም እንደሚቻል የዩኤስኤድስ ትንበያ ያመለክታል።https://flo.uri.sh/visualisation/20507494/embed?auto=1