November 30, 2024 – VOA Amharic
ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ እና በቅርቡ በሶሻል ሚዲያ የተለቀቁ ቪኦኤ ያላረጋገጣቸው የቪዲዮ ክሊፖችን በተመለከተ የፋኖ ታጣቂ ቡድን እጁ እንደሌለበት አስታውቋል።
የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ግን “የጭካኔ ድርጊት” ብለው የገለጹትንና በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ተገድሏል የተባለውን ወጣት በተመለከተ ባለፈው ሐሙስ ዕለት በጽኑ አውግዘዋል።