December 1, 2024 – Konjit Sitotaw 

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በጃል መሮ ከሚመራው ኦነሠ/ኦላ አፈንግጦ እጁን ከሠጠው ከጃል ሰኚ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ስለመፈራረማቸው ተሰምቷል ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት ተብሏል፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ  ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል። ጃል ሰኒ የተባለው ግለሰብ ከጃል መሮ ሠራዊት አፈንግጦ በግል ለብልፅግና እጁን የሰጠ ተዋጊ አመራር ነው።