December 1, 2024 

” አየር መንገዱ ላደረገው ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ  ማብራርያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ” – የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በክልሉ ትራንስፓርት እና መገናኛ ቢሮ በኩል ባወጣው መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ህዳር ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሳተፍ በተጓዙ ወገኖች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል አለ።

ይኸው የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ” ኢ-ፍትሃዊ እና አስደማሚ ነው ” ብሎታል።

ቢሮ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለፌደራል የትራንስፓርት ሚንስቴር በፃፈው ድብዳቤ እንደጠቆመው፤ ” ተቋሙ የፈፀመው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ታማኝነቱ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባት ባለፈ ሌላ ፓለቲካዊ መልክ የሚያስይዝ ነው ” ሲል አብራርተዋል።

ስለሆነም የበደላቸው ተጓዥ ደንበኞቹ እንዲክስ ፣ እንዲደግፍና ተግባሩ እንዲፈፅም ምክንያት የሆነውን በቂ ማብራርያ ለህዝብ እንዲሰጥ ቢሮው ጠይቋል።

ከአክሱም ህዳር ፅዮን በዓል ተጓዥ ተሳታፊዎች ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረገው የትኬት ጭማሪ የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር ካቢኔ መወያያ አጀንዳ እንዳደረገው ይታወሳል።