December 1, 2024 – Konjit Sitotaw
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር ሰሞኑን ባወጣው አንድ የፖሊሲ ጥናት፣ የገንዘብ ምንዛሬው ገበያ-መር መኾኑ የአገሪቱ ጥቅል ምርት ዕድገት በቀጣዮቹ ወራት በ3 በመቶ እንዲቀንስና በተለይ ከቀጣዩ ጥር ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ወራት የዋጋ ግሽበቱ ከ10 በመቶ በላይ እንዲጨምር እንደሚያደርግ ግምቱን አስቀምጧል።
ጥናቱ፣ ገበያ-መሩ ምንዛሬ የአገር ውስጥና የወጪ ምርቶች መጠን ዝቅተኛ ኾኖ እንዲቀጥል እንዲኹም የአገር ውስጥና የገቢ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር እንደሚያደርግም አመልክቷል።
ኹኔታው አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ይበልጥ መጉዳቱ አይቀርም በማለት ያስጠነቀቀው ጥናቱ፣ መንግሥት በረጅም ጊዜ የልማት ዕቅዶቹ ላይ የሚያወጣውን ወጪ በመቀነስ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የማኅበራዊ ድጋፍ መርሃ ግብሮችን እንዲቀርጽ መክሯል።