
ከ 5 ሰአት በፊት
የታንዛኒያው የተቃዋሚ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ መሪ አብዱል ኖንዶ ታፍኖ መወሰዱን በተመለከተ የአገሪቱ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
የኤሲቲ ዋዛለንዶ ፓርቲ እንደገለፈው ከሆነ ኖንዶ በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ከሚገኝ የአውቶቡስ መናኸሪያ ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍኗል ተወስዷል።
እሑድ ጠዋት አንድ ግለሰብ ነጭ መኪና ሲያሸከርክሩ በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ከአውቶቡስ መናኸሪያ መወሰዱን ፖሊስ አረጋግጧል።
የግለሰቡ ማንነት እስካሁን በይፋ ያልተረጋገጠ ቢሆንም፤ ታፍኖ የተወሰደው ግለሰብ የወጣቶቹ መሪ ነው የተባለውን እቃዎች የያዘ ቦርሳ ጥሎ መሄዱን ፖሊስ ገልጿል።
የአሁኑ ክስተት በመስከረም ወር የዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ታፍኖ መገደሉን ተከትሎ የመጣ ነው።
በመስከረም ወር የቻዴማ ፓርቲው አሊ መሐመድ ኪባኦ ከአውቶብስ ወርዶ ከተደበደበ በኋላ አሲድ ተርከፍክፎበታል። ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሃሰን ድርጊቱን አውግዘው በግድያው ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
- የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስለኢትዮጵያ ምን አሉ?1 ታህሳስ 2024
- ፕሬዝደንት ባይደን በወንጀል ጥፋተኛ ለተባለው ልጃቸው በይፋ ይቅርታ አደረጉከ 5 ሰአት በፊት
- የሶሪያን ትልቅ ከተማን ለመቆጣጠር የተቃረበው፤ ለሩሲያ እና ለአሳድ አልያዝ ያለው አማፂ ቡድን ማነው?ከ 6 ሰአት በፊት
ኤሲቲ ዋዛለንዶ እሁድ ዕለት እንደገለጸው ከሆነ ኖንዶ በቅርቡ የአካባቢ ምርጫ በሚደረግባቸው የአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍሎች ለፓርቲው ዕጩዎች ቅስቀሳ ሲያደርግ ቆይቶ ሲመለስ ታፍኖ ተወስዷል።
ፓርቲው ስጋቱን ገልጾ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
ከአፈናው ጀርባ ያለው ምክንያት ግልጽ አይደለም።